Tuesday, October 3, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአዲስ አበባ ከተማን ከጎዳና ንግድ ነፃ ያደርጋል የተባለ ዕቅድ ወጣ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በጎዳና ንግድ እየታመሱ የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ጎዳናዎችን ሥርዓት ለማስያዝ የከተማው ንግድ ቢሮ አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡

የንግድ ቢሮ ባወጣው አዲስ ዕቅድ መሠረት የጎዳና ነጋዴዎች በሚመደብላቸው ቦታ የንግድ ሥራቸውን ያካሂዳሉ፡፡ ይህን በማያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ ዕርምጃ ይወስዳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እስካሁን ከ24 ሺሕ በላይ የጎዳና ነጋዴዎች ተመዝግበዋል፡፡ ‹‹ያልተመዘገቡ የጎዳና ነጋዴዎች በከተማው ውስጥ በተለዩ 185 ቦታዎች ንግዳቸውን እንዲያካሂዱ ይደረጋል፤›› ሲሉ አቶ አብዱልፈታ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ በሥራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት የሚካሄደው ሥርዓት አልባ የጎዳና ንግድ የትራፊክ ፍሰትን ከማስተጓጎል አልፎ፣ በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ምርቶች በሰፊው እየቀረበበት እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሕጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ እስከማስወጣት የደረሰ ተፅዕኖ እያሳደረ ሲሆን፣ የከተማው አስተዳደር የጎዳና ንግድን ሥርዓት ማስያዝ እንዳለበት አስገድዷል ተብሏል፡፡

በዚህ መሠረት ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በየወረዳው እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሠረት እስከ ዓርብ መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ 24,700 የሚሆኑ ነጋዴዎች መመዝገባቸው፣ ምዝገባው እስከሚቀጥለው ወር ድረስ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት የጎዳና ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ ዕቅዶች ቢያወጣም አልተሳካም፡፡ አሁን የተጀመረው እንቅስቃሴ ምን የተለየ ነገር አለው? ተብሎ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አብዱልፈታ ሲመልሱ፣ እስካሁን 185 ቦታዎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ለመነገድ ፈቃደኛ ባልኑት ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ፣ የጎዳና ንግድ ሥርዓት መያዝ ይኖርበታል በማለት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች