Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለወጣቶች ኦሊምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ

ለወጣቶች ኦሊምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ

ቀን:

የመጀመርያው ልዑክ ሳምንት ይጓዛል

ደቡብ አሜሪካዊቷ የእግር ኳስ አገር አርጀንቲና በምታስተናግደው የዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ለመሳተፍ የተመረጠው የኢትዮጵያ ወጣት የአትሌቲክስና የብስክሌት ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻው የዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጨምሮ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች የወጣቶቹን የዝግጅት ሒደት ጎብኝተዋል፡፡

የዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በቦነስ አይረስ ከተማ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያ በአልጀርስ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ5,000 ሜትር እርምጃ፣ በ3,000 ሜትር ቀጥታ፣ በ2,000 ሜትር መሰናክልና በ800 ሜትር በሁለቱም ጾታ ሚኒማ ባሟሉ አንድ አንድ አትሌቶችና በብስክሌት ትወከላለች፡፡ አትሌቶቹ ከነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሆቴል ተቀምጠው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አትሌቶቹ የመጀመርያ የዝግጅት ምዕራፍ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉና ሌሎችም ከፍተኛ የስፖርት አመራሮች መስከረም 15 ቀን አትሌቶቹ ዝግጅት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡ ኃላፊዎቹ ወጣቶቹ ያለባቸውን ድርብ ኃላፊነት በመግለጽ የማሳሰቢያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በጉዞ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኙት አትሌቶች እዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ ውጣ ውረዶችን እንዳለፉ ያወሱት ሚኒስትሩ የአትሌቶቹ ቁጥር ምንም እንኳ ዘጠኝ ቢሆንም፣ የተሸከሙት የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ አደራ እንደሆነ ተናግረው፣ ‹‹አትሌቲክስ ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የማንነታቸው መገለጫ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ብዙ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ቀደምነት እንደነበሩት ታላላቅና ስመ ገናና  አትሌቶቻችን ሁሉ እናንተም የእነሱን  አደራና አርአያ በመከተል ኢትዮጵያውያን ከአንገታቸው ቀና የሚሉበትን ውጤትና አትዮጵያ በአትሌቲክሱ ሁሌም የማይነጥፍ ሀብት እንዳላት ማስመስከር ይኖርባችኋል፤›› በማለት ለድል እንዲበቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ መንግሥትም ለዚህ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

አትሌቲክሱ ወደ ቀድሞ ዝናውና ክብሩ ይመለስ ዘንድ ተባብሮ መሥራት ለነገ የማይባል ትልቅ ኃላፊነት እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ እስካሁን ባለው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋራ ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው ያስረዱት ፐሬዚዳንቱ፣ “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በቀደምቶቹ  ሻምበል አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋርና በሌሎቹም ታላላቅ አትሌቶቻችን ብቃት እዚህ ደርሷል፣ ያ ገናና ታሪክና ውጤታማነት በእናንተ በወጣቶቹ ላይ ነው፡፡ የተጣለባችሁ ኃላፊነት ከባድና ከእናንተ የግል ክብር በላይ ነው፣ ስለሆነም መጠንከር ይኖርባችኋል፤” ብለው “ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዕድገት፣ ለኢትዮጵያ ታዳጊዎች፣ ፕሮጀክቶች ዕድገትና መጠናከር በወጣቶቹ በእናንተ ላይ ነው፤” በማለት በተለይም በአሁኑ ወቅት አዲዳስን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ትጥቅ አምራች ኩባንያዎችና ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ስፖርት ትኩረት እንዲሰጡ ተተኪው ትውልድ  የሚያስመዘግበው ውጤት መሠረታዊ መሆኑን ጭምር ተናግረዋል፡፡

ለአፍሪካ ሴት አትሌቶች በፈር ቀዳጅነቷ የምትታወቀው ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ ‹‹በዚህ ወቅት ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት መብቃት የሩጫ ሕይወት ያለፍኩበት እንደመሆኑ ኃላፊነቱ ከባድ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ  በዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ተሳትፏችሁ የተሳካ እንደሚሆን ፊታችሁ ምስክር ነው፡፡ አርጀንቲና ሁላችንም እንደምናውቀው የእግር ኳስ አገር እንደመሆኗ፣ እኛ ደግሞ የአትሌቲክስ አገር መሆናችንን እንደምታስመሰክሩም እተማመናለሁ፤›› በማለት ሚኒስቴሩን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶቹ ያለውን አድናቆትና ክብር ገልጻለች፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...