Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባልነት 95ኛ ዓመት

የኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባልነት 95ኛ ዓመት

ቀን:

‹‹እኔ ራስ ተፈሪ፣ አገሬን ከጭለማው ዓለም ወደ ብርሃን ለማሻገር ሰላማዊ በሆነ ሪቮሊሲዮን፣ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ስለሆንኩ፣ ኢትዮጵያ የጠየቀችውን የመንግሥታት ማኅበር የአባልነት ጉዳይ ተቀብሎ እንዲፈጽምልኝ እጠይቃለሁ፡፡››

ከዘጠና ስድስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኰንን (ከቆይታ በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) በወቅቱ ለነበረው የመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦቭ ኔሽንስ) ኢትዮጵያን በአባልነት እንዲቀበል ከጠየቁበት የነሐሴ 7 ቀን 1915 ዓ.ም. ደብዳቤያቸው የተገኘ ኃይለ ቃል ነው፡፡

በ1909 ዓ.ም. የመስቀል በዓል ዕለት በተደረገ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን ባጡት ልጅ ኢያሱ ምትክ፣ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ መንበረ ዙፋኑን ሲረከቡ ራስ ተፈሪ መኰንን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴና አልጋ ወራሽ ሆነው ተሰይመዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ራስ ተፈሪ በንግሥት ዘውዲቱ ንግሥናና በባለሙሉ ሥልጣንነታቸው ስድስተኛ ዓመት ላይ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባል ሆና ተጠቃሚ መሆን ይገባታል በሚል መንፈስ ጄኔቭ ለሚገኘው የመንግሥታቱ ማኅበር የላኩት ደብዳቤ ይሁንታ ያገኘውና በአባልነት የተመዘገበችው መስከረም 17 ቀን 1916 ዓ.ም. ነበር፡፡ ይህም ማኅበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስከተመሠረተበት እስከ ጥቅምት 1938 ዓ.ም. ድረስ ዘልቋል፡፡ አልጋ ወራሹ የላኩት ደብዳቤ ይዘት እዚህ ላይ እንዳለ ከነወዙ ቀርቧል፡፡

‹‹ይድረስ ለክቡር ጀምስ ድሩሞንድ

የመንግሥታት ማኅበር ዋና ጸሐፊ፣ዤኔቭ

ሰላም ለርስዎ ይሁን

     ‹‹1. እኔ ራስ ተፈሪ መኰንን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴና አልጋ ወራሽ፣ አገሬ ኢትዮጵያን ከፌዎዳላዊ አገዛዝና ከገባር ጭቆና ሥርዓት አላቅቄ ዘመኑ የሚጠይቀውን የሥልጣኔ ዕድገት እንድታገኝ ለማድረግ ቆርጨ የተነሳሁኝ ነኝ፡፡

‹‹2. የአገሬን አስተዳደር ለማሻሻልና የሰውን ልጅ መብት ለመጠበቅ በምወስደው እርምጃ፣ ከሁሉ በፊት አገሬ ስትወቀስበትና ስትወገዝበት የቆየውን፣ ‹‹የባሪያ ንግድ›› የተባለ አስከፊ የሆነ ልምድ እስከአሁን በጀመርኩት መንገድ ከመላው የኢትዮጵያ ግዛት ለማጥፋት የማይቆጠብ ጥረት ለማድረግ የወሰንኩ ነኝ፡፡

‹‹3. አገሬ ዘመኑ በፈጠረው ሥልጣኔ ለመጠቀም እንድንችል፣ የሃይማኖትንና የመንፈሳዊን ተግባር፣ ከመንግሥት አስተዳደር መለየት አስፈላጊነቱን ስለአመንኩበት፣ ከአውሮፓ መንግሥታቶች እርዳታ ጠይቄ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መተዳደሪያ ሕገ መንግሥት ለማዘጋጀትና በተግባር ለማዋል፣ የቆረጥኩበትና ከልብ የምጥርበት ዓላማዬ ነው፡፡

‹‹4. ኢትዮጵያ በዘመናዊ ሥልጣኔ ለማስተዳደር የሚቻለው፣ አዲሱን ትውልድ በማስተማርና ለኃላፊነት በማዘጋጀት ስለሆነ፣ በአገር ውስጥ መሠረታዊ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ከማደርገው ጥረት በላይ፣ የተመረጡ ወጣቶችንም ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አውሮፓ ለመላክ የጀመርኩትን ጥረት በይበልጥ ለመቀጠል የቆረጥኩ ነኝ፡፡

‹‹5. እኔ ራስ ተፈሪ፣ አገሬን ከጭለማው ዓለም ወደ ብርሃን ለማሻገር ሰላማዊ በሆነ ሪቮሊሲዮን፣ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ስለሆንኩ፣ ኢትዮጵያ የጠየቀችውን የመንግሥታት ማኅበር የአባልነት ጉዳይ ተቀብሎ እንዲፈጽምልኝ እጠይቃለሁ፡፡››

የ፡ኢ፡መ፡አ፡ተፈሪ፡መኰንን

አዲስ አበባ ነሐሴ 7 ቀን 1915 ዓ.ም.

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...