Friday, February 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የመስቀል ሥዕል ያሉባቸው ጫማዎች በማስመጣትና በማሠራጨት የተጠረጠሩ አስመጪ ተከሰሱ

ተዛማጅ ፅሁፎች

‹‹አስመጥቻለሁ ሆን ብዬ ስላልሆነ ጥፋተኛ አይደለሁም›› አስመጪው

የወንጀል ሕግ አንቀጽ 492(ለ)ን ማለትም ‹‹ለሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚያገለግለውን ቦታ፣ ሥዕል ወይም ዕቃ ያረከሰ›› የሚለውን በመተላለፍ፣ የመስቀል ሥዕል ያለባቸውን ጫማዎች በማስመጣትና በማሠራጨት የተጠረጠሩ አስመጪ ተከሰሱ፡፡

ተከሳሹ አስመጪ አቶ ጌቱ መንጅዬ ኬራጋ እንደሚባሉ የገለጸው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ፣ ለሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚያገለግለውን የመስቀል ሥዕል ለማርከስ አስበው፣ ከፊት ለፊት ላይ በነጭ ቀለም የተሠራ የመስቀል ሥዕል ያለባቸው ሁለት ካርቶን 30 ጥንድ የወንድ ጫማዎችን አስመጥተዋል፡፡

አስመጪው ሶላቸው ላይ በቀይ ቀለም የተሠራ የመስቀል ሥዕል ያለባቸውን ዘጠኝ ካርቶኖች ወይም 135 ጥንድ የወንድ ጫማዎችን፣ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ ማስመጣታቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

ነጋዴው ቀኑ በውል ባልታወቀበት በታኅሳስ ወር 2007 ዓ.ም. በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ በጨረታ ሽያጭ ለጫማ ነጋዴዎች ማከፋፈላቸውንም አክሏል፡፡ ጫማ አከፋፋዮቹም ለሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚያገለግለውን የመስቀል ሥዕል እንዲረገጥ ያደረጉ በመሆናቸው፣ በአስመጪው ላይ ‹‹የሃይማኖትን ሰላምና ስሜት መንካት›› ወንጀል ክስ እንደመሠረተባቸው፣ ክሱን በንባብ ያሰማው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ምድብ ወንጀል ችሎት ገልጿል፡፡ ክሱ የተመሠረተው ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ቢሆንም፣ ግለሰቡ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው እስከ ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ቆይቶ ሲቀርቡ ክሱ ተነቦላቸው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

አቶ ጌቱ ድርጊቱን መፈጸም አለመፈጸማቸውም እንዲሁም ጥፋተኛ መሆን አለመሆናቸውን ተጠይቀው፣ ድርጊቱን መፈጸማቸውን (ማስመጣታቸውን) አምነዋል፡፡ እሳቸውም ክርስቲያን መሆናቸውን ተናግረው ጫማውን ያስመጡት ሆን ብለው አለመሆኑን ገልጸው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የተጠቀሰባቸው የወንጀል ሕግ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የ8,000 ብር ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲፈቱና ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል የሚላቸውን ምስክሮች አቅርቦ እንዲያሰማ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች