Wednesday, April 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በቻይናና በኢትዮጵያ መንግሥት የማሽነሪዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይገነባል ተባለ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የቻይና የኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር  በአዳማ ከተማ ለሚገነባው ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ሁናን ከተሰኘው የቻይና ግዛት የመጡ ባለሥልጣናት፣ የኩባንያዎች ፕሬዚዳንቶችና ሌሎችንም ጨምሮ 50 ያህል አባላት የተካተቱበትን ልዑክ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ባነጋገሩበት ወቅት እንደተገለጸው፣ ባንኩ በኢትዮጵያና በቻይናዋ ሁናን ግዛት መንግሥት አማካይነት ለሚገነባው የኢትዮ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ብድር ለማቅረብ ፍላጎት እንዳለውና በአፋጣኝ ብድሩ እንዲፀድቅ መንገዶችን ያመቻቻል፡፡ 

በሁናን ግዛት የኤግዚም ባንክ ቅርንጫፍ ገዥ ዋንግ ቢንግ እንደተናገሩት፣ የባንኩ ዋናው መሥሪያ ቤት ለፕሮጀክቱ የሚውለውን የብድር ገንዘብ በፍጥነት እንዲለቅ የማሳመኑን ሥራ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡

ዶ/ር አርከበ ከሁናን ግዛት ልዑካን ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት እንደገለጹት፣ ከአንድ ወር ተኩል በፊት በግዛቱ ከተገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ መካከል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርሞ ተመልሶ ነበር፡፡ በወቅቱ በተደረገው ስምምነት መሠረት ቲቢያን ኤሌክትሪክ አፓራተስ ስቶክ (ቲቢኢኤ ትራንስፎርመር ግሩፕ) እንዲሁም ሳኒ ግሩፕ ከተባሉ ሁለት ትልልቅ የቻይና ኩባንያዎች ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ በአዳማ ከተማ ኢትዮጵያ-ሁዋን የተባለና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይገነባል፡፡

በመንግሥት ይገነባል ተብሎ ከተያዘውና በዋናነት ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ይውላል ተብሎ ከሚጠበቀው በተጨማሪ፣ በቻይናና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚገነባው የሁናን ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባበት ከ300 ሔክታር መሬት በላይ መዘጋጀቱን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገቡት መካከል ሰንሻይን ግሩፕ የተባለ የቻይና ኩባንያ 80 ሔክታር መሬት ሲመደብለት፣ ኪንግደም የተባለ ኩባንያ 30 ሔክታር፣ የደቡብ ኮሪያው ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ያንግዋን ኮርፖሬሽን 200 ሔክታር መሬት ላይ የሚንጣለል የማምረቻ ግንባታ እንደሚኖራቸው አስታውቀዋል፡፡

ሲጂሲ ኦቨርሲስ ቻይና ግሩፕ የተባለውና ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአዳማ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ቁጥር ሁለት ፕሮጀክትንና የፀሐይ ሪል ስቴት ቤቶችን የገነባ ሲሆን፣ በአዳማ የሚገነባውን የሁዋን ኢትዮጵያ ማሽነሪዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክም ይኸው ኩባንያ እንደሚያከናውን ዶ/ር አርከበ አስታውቀዋል፡፡ እንደ ዶ/ር አርከበ ማብራሪያ፣ ሳኒ የተባለው ኩባንያ በዋናነት የተፈለገው በሐዋሳ የቤቶችና የንግድ ሕንፃዎች እንዲገነባ ነው፡፡ ቲቢኢኤ የተባለው ኩባንያ በአብዛኛው አገር ውስጥ የማይመረቱ ግዙፍ ትራንስፎርመሮችን የሚያመርት በመሆኑ፣ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ መስክ ላይ እንዲሠማራ የመንግሥት ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

መንግሥት በአዳማ ይገነባል ያለው የሁናን ኢትዮጵያ የማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአብዛኛው በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚያገለግሉ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ዶዘርና የመሳሰሉትን ከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች የሚመረቱበት ሥፍራ እንሚሆን አስታውቋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገመቹ በበኩላቸው፣ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ አሥር የኢንዱስትሪ ፓርኮች በግል ዘርፍና በመንግሥት ይገነባሉ ብለዋል፡፡ ለፓርኮቹ ግንባታ ከመንግሥት ካዝና፣ ከዓለም ባንክ ብድር፣ እንዲሁም ከዩሮ ቦንድ ሽያጭ በተገኘ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እስካሁን ግንባታቸው ሲካሄድ ከቆዩት ፓርኮች በተጨማሪ፣ በአዳማ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቀው ኢንዱስትሪ ፓርክ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚገነባ ይጠበቃል፡፡

መንግሥት በአንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በአማካይ ከ100 እስከ 150 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣና አንድ ፓርክ በትንሽ ከ75 ሔክታር ስፋት ባለው መሬት ጀምሮ ሊገነባ እንደሚችል ያብራሩት አቶ ፍፁም፣ በድሬዳዋ ይገነባል ተብሎ የሚጠበቀው የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ እስከ 2,000 ሔክታር መሬት ስፋት ሊኖረው እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚና ቂሊንጦ በተባሉ አካባቢዎች ከተገነቡትና እየተገነቡ ከሚገኙት በተጨማሪ በሐዋሳ፣ በመ<span style=”font-size:12.0pt;mso-bidi-font-size:11.0pt;line-height:200%;font-family: &quot;Ge” ez-1=”” numbers”,”sans-serif”‘=””>Gለ፣ በባህር ዳር፣ በድሬዳዋና በኮምቦልቻ የሚገነቡትን በአዳማ ከሚገነባው በተጨማሪ በአገር ውስጥ ወይም በውጭ የግል ኩባንያዎች ሊለሙ የሚችሉ ሌሎች ፓርኮችም ይጠበቃሉ፡፡

በሁናን ግዛት የኮሜርሺያል ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ጄነራል ሹ ሺያንግ ፒንግ የተመራው የቻይናውያን የንግድ ልዑክ፣ ጠቅላይ ሚኒትር ኃይለ ማርያምን ያነጋገረ ሲሆን፣ ለመጪዎቹ አምስት ቀናትም ከተለያዩ ሚኒስትሮች ጋር እንደሚነጋገር፣ በሐዋሳና በአዳማ ከተሞችም ጉብኝት እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

  

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች