Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአገር ውስጥ የገቡ ፓርቲዎች የተመለሱባቸው የስምምነት ነጥቦች ይፋ እንዲሆኑ ኢዴፓ ጠየቀ

አገር ውስጥ የገቡ ፓርቲዎች የተመለሱባቸው የስምምነት ነጥቦች ይፋ እንዲሆኑ ኢዴፓ ጠየቀ

ቀን:

የሥርዓት ለውጥ በኃይል ለማምጣት በትጥቅ ትግል እየታገሉ የነበሩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ከመንግሥት ጋር በመደራደር ወደ አገር ቤት ቢገቡም የስምምነቱ ዓይነትና የተስማሙባቸው ነጥቦች በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጽ ስላለበት፣ ሕዝብም የስምምነት ነጥቦችን ማወቅ ስለሚፈልግ መንግሥት በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ጥያቄ አቀረበ፡፡

ምንም እንኳን ፓርቲው መንግሥት ስላደረገው ድርድርና ስምምነት ማብራሪያ ቢጠይቅም፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄን ጨምሮ ወደ አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የገቡ ኃይሎች፣ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና ለመጫወት መመለሳቸውን እንደሚያደንቅ አክሎ ገልጿል፡፡

ነገር ግን የትጥቅ ትግል በማቆም ወደ አገር ቤት ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የተደረጉ ስምምነቶች፣ ምን እንደሆኑ መታወቅ አለባቸው ብሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በማናቸውም ለአገር፣ ለሕዝብና ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ኢዴፓ አስታውቋል፡፡

አገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረትና በአንድነት መሥራት እንዳለባቸው፣ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ ፓርቲው ገልጿል፡፡

‹‹ላለፉት ረዥም ዓመታት በአገር ውስጥ ትግል ስናካሂድ የነበርን ፓርቲዎች፣ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ ለውጥ ጭምር በመጠቀም ውስጣዊ ድክመቶቻችንን በመገምገምና ድርጅታዊ መዋቅራችንን እንደገና በመፈተሽ ራሳችንን ማጠናከር ለነገ የማንለው ድርጅታዊ ሥራ ነው፤›› በማለት ፓርቲው ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

‹‹እርስ በርስ ከመጠላለፍ በመውጣት ጠንካራ ኅብረትና ውህደት በመፍጠር የተጀመረውን ለውጥ ወደ ታለመለት ግብ ማድረስ በከፍተኛ ሁኔታ አዲስ የትግል ሐሳብ ይጠብቀናል፡፡ አሁን ባለን ድርጅታዊ አቅም በገዥው ፓርቲ ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ ማሳደርም ሆነ፣ የሕዝብን ትግል በአግባቡ መምራት የምችንልበት ደረጃ ላይ አለመሆናችንን በመገንዘብ ከየትኞችም ሥራዎቻችንን በፊት የመተባበርና የመጠናከር ጉዳይን ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል፤›› ሲል ፓርቲው አገር ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የእንተባበር ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የፓርቲዎች ተባብሮ መሥራት ዕውን ይሆን ዘንድ ሕዝቡ በጎ ግፊት እንዲያደርግ፣ ያለ ድርጅታዊ አመራርና ያለ ጠንካራ ፓርቲ የሚካሄድ የፖለቲካ ትግል የትም ሊደርስ እንደማይችል በመገንዘብ ከዚህ አንፃር ገንቢ ሚናውን እንዲጫወት እንዲሁ ለሕዝቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአገሪቱ ምሁራን፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማገዝ በአቅም ግንባታ ሥራዎችና በዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፣ የሰብዓዊ መብት መከበርን ጨምሮ የሕግ የበላይነትን ለማክበር ይቻል ዘንድ የበኩላቸውን እንዲያግዙ ኢዴፓ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...