Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናቦሌ አካባቢ በነበረ ተኩስ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

ቦሌ አካባቢ በነበረ ተኩስ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

ቀን:

ቦሌ መንገድ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚኖሩበት ሕንፃ አካባቢ መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ሌሊት በነበረ ተኩስ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የፓርላማ አባላቱ በሚኖሩበት ሕንፃ በጥበቃ ላይ የነበረ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ባልታወቀ ምክንያት ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በከፈተው ተኩስ የሦስት ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ፣ ሌሎች የፀጥታ አስከባሪዎች ጥቃቱን በፈጸመው የፖሊስ አባል ላይ ዕምርጃ በመውሰድ የአባሉ ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ አባሉ የሦስቱን ሰዎች ሕይወት ከማጥፋቱ ባሻገር፣ አሥር ያህል የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትም በፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ ታውቋል፡፡

ጥቃቱን የፈጸመው የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሊቱን ሙሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲተኩስ ስለነበር፣ አካባቢው ውጥረት ነግሶበት ማደሩ ታውቋል፡፡ በጥቃቱ ምክንያትም የቦሌ ዋና መንገድ እስከ ማለዳው 3፡00 ሰዓት ድረስ ተዘግቶ ቆይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...