Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበጥንታዊ ጽሑፎች ላይ የሚመክረው ዓለም አቀፍ ጉባዔ

በጥንታዊ ጽሑፎች ላይ የሚመክረው ዓለም አቀፍ ጉባዔ

ቀን:

ኢትዮጵያ በመንግሥታቱ ድርጅት የባህል ተቋም ዩኔስኮ ይሁንታ አግኝተው በዓለም ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱና የሚዳሰሱ ሀብቶች በተጨማሪ ከጥንታዊ የሥነ ጽሑፍና የሥነ ጽሕፈት ሀብቷ የሚቀዱ የብራና መጻሕፍትም አሉበት፡፡

በቅድመ አክሱም ከደአማት ጊዜ ጀምሮ በግዕዝና በሳባ ቋንቋዎች በድንጋይ ላይ ጽሑፍ የተጀመረው የሥነ ጽሕፈት ታሪክ በዘመነ አክሱም ከክርስትና መስፋፋት ጋር ተያይዞ በብራና ጽሑፍ በርካታ መጻሕፍት ስለመዘጋታቸውና መተርጎማቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡

ከድንጋይ ወደ ብራና ሽግግር በተደረገበት ዘመነ አክሱም (ከአራተኛው ምዕት ጀምሮ) የሥነ ጽሑፍ መነሻው የቅዱሳት መጻሕፍት ከግሪክና ሱርሰጥ ከዓረቢ ወደ ግዕዝ ተተርጉመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በስድስተኛው ምዕት ዓመት መገልበጡ የተረጋገጠው የአባ ገሪማ ወንጌል በዚህ ዘመን በጥንታዊነታቸው ከሚታወቁት ባለሥዕሎች መጽሐፍ ለመሆን በቅቷል፡፡

ይህ የጽሑፍ ቅርስ የበርካታ ምሁራንን በተለይ በባህር ማዶ ያሉትን በከፍተኛ ደረጃ ቀልባቸውን የገዛ በመሆኑ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ስለኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርሶች ሲመረምሩ፣ ጉባዔ ሲያካሂዱ ኖረዋል፡፡ የነርሱን አሠር የተከተለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የመጀመርያውን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሑፍ ቅርሶች ዙሪያ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባዔ አዘጋጅቷል፡፡ የጉባዔው መሪ ቃል ‹‹የጽሑፍ ቅርስ በምድረ ቀደምት›› ይሰኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካወጣው መርሐ ግብር መረዳት እንደተቻለው ጉባዔው ከመስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ሙሉ ቀናት በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በጉባዔው የግዕዝ፣ የዓረብኛና የአጀሚ (በዓረበኛ ፊደል በአገርኛ ቋንቋ የተጻፈ) ጽሑፍ ቅርሶች የሚመለከቱ 22 ወረቀቶች በኢትዮጵያውያንና ከአውሮፓ፣ አሜሪካና ካናዳ በሚመጡ ምሁራን ይቀርባል፡፡

በስድስተኛው ምዕት ዓመት ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ በነበሩት አባ ገሪማ አማካይነት ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተተርጉሞ የተጻፈው ወንጌል አሁን በአገልግሎት ላይ ባለው ወንጌል መካከል የተደረገ ንጽጽራዊ ጥናት ከሚቀርቡት አንዱ ነው፡፡

በግዕዝ ተመዝግቦ የሚገኘው የጊዮርጊስ ወልደ አሚድ የዓለም ታሪክ፣ የዓረቢኛ ፊደል አመጣጥ ዕድገት በኢትዮጵያ፣ በባሌ የተገኙ የዓረቢኛና የአጀሚ ጽሑፎች ጥንተ ነገር፣ በ19ኛው ምዕት በሀረር የተገኙ የአጀሚ ጽሑፎችና የሀረሪ ድርሰትም የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡

ከትቢያ እስከ ትቢያ እየጠፉ ስላሉት የኢትዮጵያ የብራና ቅርሶች ጠባቂ የሚሹ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችም የጉባዔው አንዱ ጭብጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...