በሐዋሳ እየተካሄደ ባለው 11ኛው የኢሕአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሊቀመንበር፣ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ሊቀመንበር ተደርገው ሲመረጡ፣ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር) የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሰብሳቢ ተደርገው ተመርጠዋል፡፡ በምርጫው ድምፅ ከሰጡ 177 የምክር ቤት ተሳታፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ 176 ድምፅ ሲያገኙ፣ ለምክትልነት በተሰጠው ድምፅ ደግሞ አቶ ደመቀ 149 ድምፅ አግኝተው በድጋሚ ተመርጠዋል። ከመስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የቆየው ጉባዔ ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡