Sunday, November 27, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወጣቶችን ማነጋገር ጀመሩ

  የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወጣቶችን ማነጋገር ጀመሩ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከከተማው ወጣቶች ጋር መነጋገር ጀመሩ፡፡

  ምክትል ከንቲባው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከቦሌና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር መነጋገራቸው ታውቋል፡፡

  በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተቀሩት ስምንት ክፍላተ ከተማ ወጣቶች ጋር እንደሚነጋገሩ፣ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

  እስካሁን በሁለት ክፍላተ ከተሞች የተካሄዱ ውይይቶች ሁሉንም የአዲስ አበባ ወጣቶች ያካተተ ካለመሆኑም በላይ፣ ተሰብሳቢዎቹ ለውይይት የተጠሩበት አኳኋን ግልጽ አይደለም የሚል ቅሬታ እየቀረበ ነው፡፡

  ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ወጣቶቹን ለውይይት የሚጋብዙት የክፍለ ከተማ መዋቅሮች ሲሆኑ፣ ምክትል ከንቲባው ከሚመለከታቸው የካቢኔና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ስብሰባውን ያካሂዳሉ፡፡

  በቦሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የወጣቶች ውይይት ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ያለ ግንባታ ለዓመታት ታጥረው የነበሩና የከተማ አስተዳደሩ የሊዝ ውል አቋርጦ ወደ መሬት ባንክ ያስገባቸው ቦታዎች ለወጣቶች እንዲሰጡ፣ ወጣቶች እየገጠማቸው ያለው የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታ፣ ወጣቶች ብሔር፣ ቋንቋና ሃይማኖት ሳይለያቸው እየኖሩ ሳለ ሊከፋፍሉ የሚፈልጉ ኃይሎች ስላሉ መንግሥት ዕርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቁ ናቸው፡፡

  በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ውይይትም እንዲሁ ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ በተለይ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲወገዱ፣ ወጣቶች ተደራጁ እየተባሉ ከተደራጁ በኋላ ዞር ብሎ የሚያያቸው እንደሌለ፣ ሼድ ከተሰጣቸውም ሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮች እንደማይዘረጉላቸው አውስተዋል፡፡ በልማት የሚካሄድ ማፈናቀል እንዲቆም ወጣቶች ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

  ምክትል ከንቲባው በሰጡት ምላሽ የወጣቶችን ጥያቄ ሰምተው ዝም ብለው ከንፈር መጠው እንደማይሄዱ ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ነገር ግን ሁሉም የተነሱት ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ ይመለሳሉ ማለት ግን አይደለም፡፡ ጥያቄዎቹ በየደረጃው እንደሚፈቱና ወጣቶች ግን የከተማውን ሰላምና አንድነት በማስጠበቅ ረገድ መሥራት አለባቸው፤›› ሲሉ ምክትል ከንቲባ ታከለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡    

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...