Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየታዳጊዎቹ ተሰጥኦና ችሎታ በእስራኤላዊው እግር ኳሰኛ ዕይታ

  የታዳጊዎቹ ተሰጥኦና ችሎታ በእስራኤላዊው እግር ኳሰኛ ዕይታ

  ቀን:

  እግር ኳስ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ እንዳልሆነ ለመረዳት ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በየሠፈሩ ከመኪናና መሰል ነገሮች ጋር እየተጋፉ ኳስ የሚያንከባልሉ ታዳጊዎችን መመልከቱ በቂ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያውያኑ ታዳጊዎች ተሰጥኦና ችሎታ በበቂ እግር ኳሰኛ ሙያተኞች ታግዞ ለውጤት ሲበቃ እየታየ ግን አይደለም፡፡ ለዚህ የዘርፉ ሙያተኞች የየራሳቸውን መላምት ከማስቀመጥና ምክንያት ከመደርደር ባለፈ ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት አለመቻላቸው ምክንያት ተደርጎም እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡ አስተያየቱን ከሚጋሩት ውስጥ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ደግሞ እስራኤላዊ የሆነው አቶ ቻላቸው ምሕረቱና የሙያ አጋሩ አቶ ዮሴፍ ገብረአምላክ ይጠቀሳሉ፡፡

  በጎንደር ከተማ ተወልዶ በስድስት ዓመቱ ወደ እስራኤል ማምራቱን የሚናገረው አቶ ቻላቸው እስራኤላዊ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ለ25 ዓመታት ያህል ከትውልድ አገሩ ርቆ መቆየቱን ያስረዳል፡፡ በእስራኤል ዕድሜው 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ አቡል ሐይፋ ለሚባል ክለብ በፕሮጀክት ታቅፎ መሠረታዊ የእግር ኳስ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ፣ ለሦስት ዓመት ያህል የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ ቀጥሎም ወደ ቀድሞ የእግር ኳስ ሕይወቱ ተመልሶ ራማት እስራኤል ለሚባለው ክለብ ለአምስት ዓመት መጫወት መቻሉንና ከዚያም ከአንድ የሥራ ባልደረባው ጋር በመሆን ‹‹በኔ ይቻላል›› የሚባል የእግር ኳስ ፕሮጀክት አቋቁሞ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ከሦስት ዓመታት በፊት ማለትም በ2005 የውድድር ዓመት ለጉብኝት ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮጵያ ተመልሶ ሳለ መገናኛ ላምበረት አካባቢ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች መንገድ ዳር በሚያደርጉት የእግር ኳስ እንቅስቃሴ መደነቁንና እስከወዲያኛው ሐሳቡን ለመቀየር የተገደደበት አጋጣሚን የፈጠረለት መሆኑን ያስረዳል፡፡

  እስራኤላዊው እግር ኳሰኛ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሱ በፊት ወደ አውሮፓ በማቅናት የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የሚሰጠውን የአሠልጣኝነት ኮርስ ወስዶ ዲፕሎማ ማግኘቱንም ይናገራል፡፡ ሙያተኛው በኢትዮጵያ የጥቂት ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላ በመጣበት በ2005 የውድድር ዓመት ወደ እስራኤል በማቅናት ለሁለት ዓመታት ያህል ከቆየ በኋላ የነበረውን መጠነኛ ጥሪት በመያዝ እንደገና በ2007 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡ በዚያው ዓመት ከአቶ ዮሴፍ ገብረአምላክ ጋር በመሆንም ‹‹አዲስ ዘመን የታዳጊዎች እግር ኳስ ፕሮጀክት›› በሚል መጠሪያ ከስድስት ዓመት ጀምሮ እስከ 17 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 30 ታዳጊ ወጣቶችን በመያዝ የዕቅዱን የመጀመርያ ምዕራፍ አንድ ብሎ መጀመሩን ይናገራል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የታዳጊ ወጣቶቹ ብዛት 300 የደረሰ ስለመሆኑም ያስረዳል፡፡

  ሁለቱ ሙያተኞች የታዳጊ ወጣቶቹ ተፈጥሯዊ ተሰጥኦና ችሎታ እንደተጠበቀ፣ ይኼ ሁሉ እምቅ የእግር ኳስ ሀብት ባለበት አገር በየካፌውና መዝናኛ ቤቱ ስለአገሪቱ የእግር ኳስ ውድቀት ሲነገር ማድመጥ በተለይ ለአቶ ቻላቸው የሚታመን እንዳልሆነ ያስረዳል፡፡ ፕሮጀክቱ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአዲስ አበባ እግር ኳስ ሥር በ‹‹ቢ›› ደረጃ ተመዝግቦ በዓመታዊው የውድድር መርሐ ግብር እየተሳተፈ እንደሚገኝም ይናገራል፡፡

  ለፕሮጀክት የሚውለውን በጀት በተመለከተም በአቶ ቻላቸው ምሕረቱ ካልሆነ በአሁኑ ወቅት ሊጠቀስ የሚችል ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ እንደሌለው፣ ሆኖም የታዳጊ ወጣቶቹ ወላጆች ልጆቻቸው የተሻለ ደረጃ ይደርሱላቸው ዘንድ አቅማቸው የፈቀደውን እንዲያደርጉ መደረጉንም ይናገራሉ፡፡ እንደ ሁለቱ ሙያተኞች ከሆነ ትልቅ ደረጃ ይደርሳል ተብሎ ለሚጠበቀው ለዚህ የእግር ኳስ ፕሮጀክት በመሠረታዊነት ሊታሰብ የሚገባው ሕዝባዊ አደረጃጀት ይኖረው ዘንድ መሥራት እንደሚያስፈልግ ነው የሚያምኑት፡፡

  ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤምባሲ ማኅበረሰብ ክፍሎች ከሚያዘጋጁት ዓመታዊ ውድድር ጎን ለጎን ለፕሮጀክቱ በገንዘብ ሳይሆን የአልባሳት እገዛ በቼክ ኤምባሲ አማካይነት እንደተደረገለት፣ ለዘለቄታው ግን ሰኔ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ለዚሁ ፕሮጀከት ገቢ ማስገኛ የእራት ግብዣ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና በዋናነትም ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጋር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ የፕሮጀክት ስምምነት ማድረጋቸውን ያስረዳሉ፡፡

  በመጨረሻም አዲስ ዘመን የታዳጊዎች ፕሮጀክት በቀጣይ የተሻለ ደረጃ ይደርስ ዘንድ ከክለቦች ጭምር የሚመለከታቸው አካላት የሚችሉትን ድጋፍና ክትትል ሊያደርጉለት እንደሚገባ፣ እንዲሁም እንደነዚህ ለመሰሉ ፕሮጀክቶች ዋንጫና መሰል ሽልማቶችን ከማዘጋጀት ይልቅ በፕሮጀክቱ ለመሳተፍ ታዳጊ ወጣቶች ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ለትምህርታቸው አጋዥ የሚሆኑ ስጦታዎች በሽልማት መልክ ቢዘጋጁ ሁሉም ሰው ለትክክለኞቹ ታዳጊ ወጣቶች ትኩረት እንዲሰጡ እንደሚያደርግ ይመክራሉ፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...