አስፈላጊ ጥሬ ዕቃ
- 1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት (ዘይቱ የመረጡት ሊሆን ይችላል)
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ በሶቢላ (እርጥብ)
- 2 የተከተፈ ቲማቲም
- 1 በቀጫጭኑ የተከተፈ ትልቁ ቃሪያ
- 2 እግር መሽሩም የተከተፈ
- 1 ራስ ቀይ ሽንኩርት በስሱ የተከተፈ
- 4 ድንች በትናንሹ የተከተፈ
- ከተለያዩ አትክልቶች የተሠራ ሾርባ 300 ሚሊ ሊትር
አዘገጃጀት
- በትልቅ መጥበሻ ዘይቱን ጨምሮ ማጋል
- የተከተፈውን መሽሩም፣ ቃሪያ፣ ሽንኩርትና ድንች ጨምሮ ለአምስት ደቂቃ ማብሰል
- ሲበስል የተዘጋጀውን ሾርባ፣ በሶቢላ፣ ቃሪያና ጨው ጨምሮ ለሦስት ደቂቃ ማብሰል
- በመጨረሻም የሎሚ ጭማቂውን ጨምሮ ጨውን በማስተካከል ማውጣት
- ይህ ስጎ በዳቦ ሊበላ ይችላል፡፡ ለሩዝ፣ ፓስታና መኮሮኒ መጠቀምም ይቻላል፡፡
ቢቢሲ ጉድ ፉድ ድረገጽ