Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናፓርላማው ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

  ፓርላማው ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

  ቀን:

  ፓርላማው ለአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና ለሴቶች የንግድ ሥራ ፈጠራ የሚውል ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ፡፡

  ለአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ የልማት ፕሮጀክቶች ከዚህ ቀደም 195 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ተገኝቶ ፕሮጀክቶቹ የተጀመሩ ሲሆን፣ ፓርላማው ማክሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ያፀደቀው ከዓለም አቀፍ የግብርና ፈንድ የተገኘን 15 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡

  የአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ የልማት ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ሦስተኛ ዙር ላይ ደርሷል፡፡ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሶማሌና አፋር ክልሎች በሚገኙ 113 ወረዳዎች የሚተገበር ነው፡፡

  ፕሮጀክቱ ለዘመናት ከማናቸውም የኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ተገልለው የቆዩ አርብቶ አደሮችን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻልና የአደጋ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን ድጋፍ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

  በሌላ በኩል ፓርላማው ከጣሊያን መንግሥት የሴቶች የንግድ ሥራ ፈጠራ ብቃትን ለማሳደግ የሚያስችል 15 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አፅድቋል፡፡

  የሴቶች የንግድ ሥራ ፈጠራ ብቃትን ለማሳደግ መንግሥት ለቀረፀው ፕሮጀክት፣ የዓለም ባንክ ከዚህ ቀደም 50 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዚህ ቀደም ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ ገንዘብ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል በመልሶ ማበደር ሥርዓት በሴቶች ለሚቀረፁ ፕሮጀክቶች በማበደር ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡

  በጣሊያን መንግሥትም የቀረበው ብድር ለዚሁ ዓላማ የሚውል ነው፡፡ በተመረጡ ከተሞች የሚገኙ በከፊልም ሆነ በሙሉ በሴቶች ይዞታ ሥር ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ገቢ የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...