Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር የ250 ይዞታዎችን ካርታ አመከነ

  የአዲስ አበባ አስተዳደር የ250 ይዞታዎችን ካርታ አመከነ

  ቀን:

  ፖሊስ ጋራዥ ከሸራተን ማስፋፊያ ላይ ተነሳ

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ግንባታ ያልተካሄደባቸውን 250 ይዞታዎች ካርታ በማምከን ወደ መሬት ባንክ ገቢ አደረገ፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማቶች ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይለ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በወቅቱ ግንባታ ያላካሄዱ አልሚዎች ላይ በዘመቻ መልክ ዕርምጃ ተወስዷል፡፡ ዕርምጃው በዘመቻ ሊወሰድ የቻለው ቀደም ብሎ መወሰድ የነበረባቸው ዕርምጃዎች ባለመውሰዳቸውና ሥራውም በመከማቸቱ ነው ብለዋል፡፡

  ‹‹ከዚህ በኋላ ግን በወሰዱት መሬት ላይ ግንባታ በወቅቱ በማያካሂዱ አልሚዎች ላይ የሚወሰደው ዕርምጃ በዘመቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ሥራ ይሆናል፤›› በማለት አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ አቶ ሰለሞን ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን በሁለት ከፍለው አስረድተዋል፡፡ የመጀመርያው የከተማው አስተዳዳር መሬት ሙሉ በሙሉ አፅድቶ ያላስረከባቸውና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዕግድ ወጥቶባቸው በሕግ ሒደት ላይ ያሉ ሲሆኑ፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አፅድቶ ቢያስረክብም ባለሀብቶቹ ግን ወደ ግንባታ ባለመግባታቸው ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ናቸው፡፡

  ‹‹በአስተዳደሩ ችግር ወደ ግንባታ ላልገቡት አስተዳደሩ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ ነገር ግን በራሳቸው ችግር ወደ ግንባታ ያልገቡት ላይ ግን ዕርምጃ ይወስዳል፤›› በማለት አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡

  ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በይዞታ በኩል የሚወስዳቸው ዕርምጃዎች አድሏዊ መሆናቸውን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ አስተዳደሩ በዝቅተኛ ማኅበረሰብ ይዞታዎች ላይ ጠንካራ ክንዱን ሲያሳርፍ፣ ከፍተኛ ገቢ ባለው ማኅበረሰብ ላይ ግን ተመሳሳይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በርካቶች ይተቻሉ፡፡

  ለዚህ የሚያቀርቡት ምክንያት በሚድሮክ የተያዙ ደረጃ አንድ ቦታ ላይ የሚገኙ መሬቶች እስከ 18 ዓመት ድረስ ታጥረው መቀመጣቸውን ነው፡፡ በተለይ ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት፣ አራት ኪሎ (ፊት በር) ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት፣ ካዛንቺስ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጎን፣ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎንና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 13 ቦታዎች አራት ከንቲባዎች ቢፈራረቁም ያለ ግንባታ ታጥረው መቀመጣቸው እስካሁን አነጋጋሪ ናቸው፡፡

  አቶ ሰለሞን ይህን በተመለከተ ሲያብራሩ፣ ‹‹ሚድሮክ ወደ ግንባታ ያልገባባቸው በርካታ ምክንያቶች ነበሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የነበሩት ችግሮች በሙሉ ተፈተዋል፡፡ ሚድሮክ ከወራት በፊት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ ወደ ሥራ ካልገባ የሚወሰደው ዕርምጃ በቀጣይ ይታያል፤›› ብለዋል፡፡ ለሸራተን አዲስ ማስፋፊያ በአራዳና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 42 ሔክታር መሬት ተሰጥቷል፡፡

  የሸራተን ማስፋፊያ በሆነው 42 ሔክታር መሬት ላይ የነበሩ ነባር መንደሮች ከአራት ዓመት በፊት ፈርሰዋል፡፡ ነገር ግን የፌዴራል ፖሊስ ጋራዥና ማዘዣ ጣቢያ ከቦታው ላይ ባለመነሳታቸው ሚድሮክ ወደ ሥራ መግባት እንዳልቻለ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

  ሆኖም በአሁኑ ወቅት ፌዴራል ፖሊስ ከሥፍራው ላይ መነሳቱ ተጠቁሟል፡፡ ‹‹ፖሊስ ባለመነሳቱ ልማቱ መቆም ነበረበት? ወይስ የለበትም? የሚለው ሌላ ነገር ሆኖ፣ አልሚው ፖሊስ ካልተነሳ መሥራት አልችልም ስላለ እስኪነሳ ተጠብቋል፡፡ አሁን ግን ቦታው ሙሉ ለሙሉ ፀድቷል፤›› በማለት አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...