Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዋሊያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለቻን ዝግጅት ምን ያስተምራል?

የዋሊያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለቻን ዝግጅት ምን ያስተምራል?

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በአራተኛው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በኬንያ አቻው 3 ለ 0 መረታቱ ይታወሳል፡፡ ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታድየም በጨዋታ በልጦ ግብ ማግባት የተሳነው ብሔራዊ ቡድኑ በመልሶ ጨዋታ ሰፊ ግብ ይቆጠርበታል፣ የዋዠቀ እንቅስቃሴም ያሳያል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡

በወቅታዊው የእግር ኳስ ደረጃ አንፃር ኬንያ ያለችበት ደረጃ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እምብዛም እንዳልሆነ ግን ዋሊያዎቹ የነበራቸው ደካማ ጎን መጠቀማቸው የተሻሉ እንዳደረጋቸው ተገልጿል፡፡ በሦስት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ በቡድን ሲያጠቁና ሲከላከሉ የተስተዋሉት የሐራምቤ ከዋክብት፣ በሜዳቸው ውጤቱን መቀየር እንደሚችሉ ከጨዋታቸው ቀድሞውንም በመታዘብ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስረዱ ነበር፡፡

ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ መድረክ ለመሳተፍ ዝግጅት ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ ከሚያደርጋቸው የምድብ ጨዋታዎች የሚታዩ ክፍተቶች ሲደጋገሙ ቡድኑ ረጅም ጊዜ ወስዶ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርበት ሲገለጽ ከርሟል፡፡

ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈበት ጊዜ አንስቶ ብሔራዊ ቡድኑ ያደረጋቸውን የምድብ ጨዋታ ለተመለከተ ሰው ብሔራዊ ቡድን ክፍተቱን እያረመ እንዳልመጣ ያስረዳል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከአምስት ያላነሰ አሠልጣኝ የተቀጠረለት ብሔራዊ ቡድን መሠረታዊ ችግሮቹን ሲያሻሽል አለመታየቱ ባለሙያዎች ያብራራሉ፡፡

አዲሱ የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ የቅጥር ስምምነታቸውን ባከናወኑበት ወቅት ብሔራዊ ቡድኑን ለ2020 የቻን ውድድር ውጤታማ ማድረግ ቀዳሚ ሥራቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ቡድኑ ይዞት ከመጣው ወጥ ያልሆነ የዝግጅት ባህል አንፃር ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶና የተስፋ ቡድን መሥርቶ ዝግጅቱን እንደ አዲስ መጀመር እንዳለበት ይነገራል፡፡

አዲስ አሠልጣኝ በመጣ ቁጥር ተጨዋቾችን ለብሔራዊ ቡድን እየጠሩና እየተበተኑ መጓዝ የእግር ኳሱን ደረጃ ከማሽቆልቆልም በላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ ባለሙያዎች ሲተቹ ይደመጣል፡፡ ለዚህም ተደጋጋሚ ችግር ብሔራዊ ቡድኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ባለማድረጉና የይድረስ ቡድን ምሥረታ ላይ ትኩረት ማድረጉ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ ኢትዮጵያ የ2020 የቻን ውድድር ለማሰናዳት ከካፍ ኃላፊነት መረከቧ ይታወሳል፡፡ ዝግጅቷን በተመለከተ ካፍ አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይኼን ተከትሎ ብሔራዊ ቡድኑም አዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን በቀሩት ጊዜያት ወገቡን ጠበቅ ማድረግ እንደሚገባ ይመከራል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመርያውን ማጣሪያ በምድቡ ከሚገኘው ጋና 5 ለ 0 ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ በተጨዋቾች ላይ የሥነ ልቦናዊ ጫና እንዳረፈበት ይነገራል፡፡  በሐዋሳ ስታዲየም የሴራሊዮን አቻውን 1 ለ 0 ከረታ በኋላና በባህር ዳር ስታዲየም ያሳየው እንቅስቃሴ የመጀመሪያውን ጨዋታ ማዘንጋቱ አልቀረም፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ የታዩበትን ክፍተቶች ለመሙላት ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዕርዳታ ማድረግ እንዳለበት የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የተለያዩ ትችቶች ከዳር እስከዳር ቢሰነዘሩም ችግሮች ግን መፍትሔ አለመገኘቱ ችግሩን እንዳከፋው የሚጠቅሱ አሉ፡፡

በፕሪሚየር ሊግና ብሔራዊ ሊግ ላይ ያለው ፉክክር እየጨመረ ቢመጣም፣ ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ግን የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም እየተሳነው መምጣቱ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠበቅበታል፡፡

ምድብ ስድስት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአራት ነጥብና በሰባት የግብ ዕዳ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ተቀምጧል፡፡ ቡድኑ ከጋናና ከሴራሊዮን የሚያደርገው ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞውን ይወስናል፡፡

በጥር ወር በሚካሄደው የካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ ዕድሉ የመርፌ ቀዳዳ የሆነበት ቡድኑ ከወዲሁ ችግሮችን በማረም ለቻን ውድድር መዘጋጀት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ አስተያየታቸውን የሚሰነዝሩ አልታጡም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...