Friday, May 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአገራዊው ሰንደቅ ዓላማ

አገራዊው ሰንደቅ ዓላማ

ቀን:

«በባንዲራ!! በባንዲራ!! በባንዲራችን!! በሕግ ቁም ብዬሃለሁ!!» ትለዋለች፤ እየተከተለች፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ፣ ወደ ቀጨኔ መድኃኔዓለም በሚወስደው መንገድ፣ ድልድዩ አጠገብ፣ ከአባ ሀብቴ ቤት አጠገብ ነው፡፡ ሴትየዋ ጠላ ሻጭ ናት፡፡ ሰውዬው እግረ መንገዱን ሲያልፍ ጠላ ሊጠጣ ይገባና ሳይከፍል ይወጣል፡፡ እሷ እንዳለችው ሁለት «ምኒልክ» ነው የጠጣው፡፡ምኒልክ» የጠላ መጠጫ ዋንጫ ነው) እሱ ደግሞ «የለም አንድ ብቻ ነው» ይላል፡፡ የጎረቤት ሰው ጠርቷት ወጣ ብላ ተነጋግራ እስክትመጣ ድረስ ሰውዬው ከእንስራው ውስጥ ቀድቶ ሁለተኛውን «ምኒልክ» እሷ ሳታየው ጠጥቷል፡፡ እሷ ግን ሁለተኛ መጠጣቱን ደርሳበታለች፡፡ ሲወጣ የአንድ ምኒልክ ሒሳብ ከፍሎ ይወጣል፡፡ ጎረምሳ፣ ሰውነቱ ዘለግ ያለ ነበር፡፡ ሴትዮዋ ደግሞ ቀጭን፣ ኮሳሳ ድሀ ነች፡፡ ጥንካሬዋ ግን ባንዲራ ነበር፡፡

«በባንዲራ!! ወድቃ በተነሳችው!!» ብላ በጮኸች ቁጥር ኩራትና ጥንካሬ ይሰማታል፡፡ በሌላ በኩል እየተከተለች «በባንዲራባለችው ቁጥር ሰውዬው እያነሰ፣ እየኮሰሰ ሄደ፡፡ መንገደኛው ሁሉ «ምንድነው ይህ ሰውዬ በባንዲራ ሲባል አይሰማም እንዴ?» እያለ ሰውየውን ትኩር ብሎ ያየው ጀመር፡፡

ሰውዬው ግራ ገባው «ይህች ኮሳሳ ደሃ እንዲህ ታዋርደኝ?» ይላል በልቡ፡፡ የወንድነት ወኔው፣ የጎረምሳ ኩራቱ እያሸነፈው ለመቆም በጣም አመነታ፡፡ ዝም ብሎ ቢሄድ የሚያስከትለውን ነገር ባለማወቁ መሀል መንገድ ላይ ቀጥ ብሎ ቆሞ ከኪሱ ስሙኒ ፈልጐ ወረወረላትና መንገዱን ቀጠለ፡፡ ባንዲራዋ አሸነፈች፡፡

- Advertisement -

ይህ መንደርደርያ ሐተታ ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲነሳ፣ ሲወሳ ከተመዘገቡት ትዝታዎችና ገጠመኞች አንዱ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ገጠመኝ በመስከረም 1999 ዓ.ም. በአሜሪካ ከታተመው የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ‹‹ክህደት በደም መሬት›› መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሯል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ሌላው ስሙ ከጣሊያንኛ የተወሰደው ባንዲራ ነው፡፡

ከትናንት በስቲያ ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲዊ አንድነታችን›› በሚል መሪ ቃል በፓርላማ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በተገኙበት የተከበረውን 11ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግም ዝክረ ሰንደቅ ዓላማን እንዘልቅበታለን፡፡

የሰንደቅ ዓላጅማሮ

በቀደመው ጊዜ ስለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ታሪካዊ አመጣጥና ትርጓሜ ከጻፉት በርካታ ጸሐፊዎች አንዱ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩት ፓሻ ኃይለማርያም ሰራቢዮን ናቸው፡፡ 1898 . «የኢትዮጵያ ትእምርተ መንግሥት» በሚል ርእስ ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚናገር በሚለው ምዕራፍ በገጽ 18 ላይ እንደሚከተለው ጽፈዋል፡፡

«ሰንደቅ ዓላማ ማለት የንጉሥና የሕዝብ ምልክት ነው፡፡ የዓለም ነገሥታትና ሕዝብ እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ የወዴት አገር ንጉሥ ነው? ይህ የወዴት አገር ሕዝብ ነው እንዳይባል ልዩ ልዩ ሰንደቅ ዓላማ ያሲዛሉ፡፡ በበዓል ቀንም በየደጃቸው ይሰቅላሉ፡፡ ይህንም ያየ ሰው ሁሉ የእገሌ አገር ንጉሥ ነው፡፡ ይህ የእገሌ አገር ሕዝብ ነው ብሎ በሰንደቅ ዓላማው ያውቀዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማውም እጅግ ይከበራል፡፡ ሲሰቀልና ሲወርድም በዜማና በሰላምታ ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማውን ያየ ሰው ሁሉ ቆቡን፣ ባርኔጣውን ያወርዳል፡፡ አለቆችም ሰይፍ ይመዛሉ፡፡ በሰልፍና በጦርነት በጸሎትና በፍሥሐ ቀንም ያለሰንደቅ ዓላማ አይሆንም፡፡ የክብር ሁሉ መሠረት ነውና፡፡ በጦርነት ጊዜም ንጉሡ ራሱ ሰንደቅ ዓላማውን በእጁ ይዞ ለጦር አበጋዙ አደራ ይሰጠዋል፡፡ እንዲህ ሲል በርታ አደራህን ሰንደቅ ዓላማችን በጠላት እጅ እንዳይገባ፡፡ እኛና ሕዝባችን እንዳንዋረድ፣ ክብራችን እንዳይጠፋ የጠላት መሳለቂያ እንዳንሆን አደራህን ይለዋል፡፡»

አለቃ ደስታ ተክለወልድ በ1962 ዓ.ም. ባሳተሙት በዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ሰንደቅ ዓላማን ‹‹በሰንደቅ ላይ የተሰቀለ የተንጠለጠለ ባለ አረንጓዴና ቢጫ፣ ቀይ ቀለም፣ የመንግሥት ምልክት ባንዲራ›› ብለው ይፈቱትና በመካከሉ ጽሑፍና የአንበሳ ሥዕል ከዘውድ ጋራ እንደሚታይበት አንበሳውም ሰንደቅ ዓላማ መያዙን ያሳያሉ፡፡

በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው ሌላ የማዕከላዊ መንግሥት መዲና ጎንደር በነበረበት ወቅት 1660 እስከ 1674 ዓ.ም. የነገሡት አፄ አዕላፍ ሰገድ ዮሐንስ፣ በጎጃም ለምትገኘው ደብረ ወርቅ ማርያም በሰጧቸው ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች ቅርፃቸው፣ ይዘታቸው የቀለማቸው ዓይነትና አቀማመጥ ዛሬ ያለው ሰንደቅ ዓላማ ዓይነት እንደሆነ የሚረጋገጥ ለመሆኑ 1939 ዓ.ም. በወጣውናሰላማዊ ሰልፍና ውስጣዊ አሠራርበሚለው ሰነድና በንጉሡ ዜና መዋዕል ተዘግቦ ይገኛል፡፡

በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመ1936 .ም. የወጣው የኢትዮጵያ ገንዘብ ኖት፣ 1992 . የቀለማት ቅደም ተከተሉ እስከተለወጠበት ድረስ የሰንደቅ ዓላማውን ታሪክና ምሳሌነት የያዘ ነበር፡፡ አንደኛነትን ለባለ አንድ ብር አረንጓዴ ኅብር የመሠረት ምሳሌ፣ ሁለተኛነትን ለባለ አምስት ብር ቢጫ ኅብር የሕንፃ ምሳሌ፣ ሦስተኛነትን ለባለ አስር ብር ቀይ ኅብር የጠፈር ምሳሌ አቅፏል፡፡

በአክሱም ያለው ጥንታዊው ዓላማ አረንጓዴው በታች ቀዩ ግን በላይ ሆኖ ሦስቱም ቀለማት ሁሉ ለእያንዳንዱ ጫፍ የሾለ ማለት ሦስት ጦር የሚመስል ሆኖ የተሰፋ መሆኑ ይነገራል፡፡ በተለይ 1897 .ም. የቀለማቱ ድርድር አረንጓዴው ከላይ ቀዩ ከታች ሆኖ ከተሰደረበት ወዲህ ላለፉት 114 ዓመታት መደበኛ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

የኅብረ ቀለማቱ አቀማመጥ በየጊዜው ቢለዋወጥም በአፄ ዮሐንስ አራተኛ ዘመን በሕግ መደበኛ የነበረው ከላይ ቀይ ከሥር አረንጓዴ እንደነበረና በ1879 ዓ.ም. በዶጋሊ ጦርነት በራስ አሉላ አዝማችነት በጣሊያን ላይ በተቀዳጁት ድል ሲውለበለብ የነበረው ሰንደቅ ዓላማ እርሱ መሆኑ ይነገራል፡፡ የአፄ ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ በጎንደር ሲገኝ መስቀያው ሰማያዊ በዓላማውም ላይ «የይሁዳ አንበሳ» የሚለው የአንበሳ ሥዕል በቀኝ መዳፉ ሰንደቅ ዓላማውን ከነመስቀላዊ ምልክትነቱ እንደተሸከመ ተጠልፎበታል፡፡

1884 .ም. ሶለይለት የተባለ መልእክተኛ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በተደረገለት ስጦታና ሽልማት በቀይ በነጭ በቢጫና በአረንጓዴ ኅብረ ቀለማት ላይ የተጠለፈ ኮከብ ጥብጣብ እንደቀረበለት ጠቅሷል፡፡ 19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ የቀጣዩ መባቻ አካባቢ በባቡር ኢትዮጵያ ገብቶ የነበረው ጆኒንግስ በጻፈው ማስታወሻ ላይ «ከዘጠነኛው ኪሎ ሜትር አቅራቢያ በሚገኝ ቋጥኛማ ኮረብታ ላይ ቀይ፣ ቢጫ እና አረንጓዴ ኅብረ ቀለም ያለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሰላምታውን አቀረበልን…» ብሎ ጥቅምት 29 ቀን 1903 . መጻፉን አቶ ማሞ ውድነህ በአንድ ጥናታቸው ገልጸውታል፡፡

የቀለማት ትርጉም

በፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ላይ እንደተገለጸው አረንጓዴው የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው። ቢጫው ደግሞ የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ሲሆን ቀዩ ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡

በቀድሞ ጊዜ የዚሁ ሰንደቅ ዓላማ ኅብረ ቀለማት ምሳሌያቸው አረንጓዴው ተስፋ ልምላሜና ሀብት፤ ቢጫው ሃይማኖት አበባና ሬ፣ ቀዩ ፍቅር መሥዋዕትነትና ጀግንነት ነበር፡፡

ዓርማ

በሰንደቅ ዓላማው ላይ በአገሪቱ በተከሰቱ መንግሥታት ባሕርይ ዓርማ ሲጠለፍበት ኖሯል፡፡ በዘውዳዊው ሥርዓት የአንበሳ ምልክት፣ በኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኢትዮጵያ ሽግግር መንግሥታት የየራሳቸው ዓርማዎች ነበሯቸው፡፡ የአሁኑ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዓርማ ባለ አምስት ኮከብ ሰማያዊ ቀለም ከዓላማው ጋር ተቀናጅቶ አካሉ ሆኗል፡፡

ከሰንደቅ ዓላማው አጀማመር ጋር የተያያዘቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም በሥላሴ በመሰለችው ሦስቱ ኅብረቀለማት ላይ፣ «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» (እነሆ የመንግሥት ወንጌል) የሚል ሐረግና የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓርማ የተጠለፈበት ሰንደቅ ዓላማም አላት፡፡

በጥንት ዘመን ስለነበረው ዓርማ በተመለከተ አቶ ዘመንፈስ ቅዱስ የታሪክ ቅርንጫፍ በሚለው ድርሳናቸው ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡- «በቢጫው (መካከለኛ) ላይ በአንድ ወገኑ በወርቅ የተጠለፈ አንበሳ አለው፡፡ ከባለታሪኮች አፍ  እንደሰማሁትም በሌላኛው ወገኑ ደግሞ በወርቅ የተጠለፈ ፈረስ ነበረው ይባላል፡፡ ይህም የሚያመለክተው የጥንታውያኑ ነገሥታት ዋናው ኃይላቸው በፈረስ ብዛትና በፈረሰኛ ኃይል ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል አድርገው እንደ አንበሳ ይፈሩ እንደነበሩ የሚያስረዳ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህንኑ መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ነገሥታት ማኅተማቸውን ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ (አሸናፊው የይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ) እያሉ ኖረዋል፡፡

የሕዝብ መዝሙር

በቀደመው ጊዜ ከሰንደቅ ዓላማ ክብር ጋር አብሮ ተያይዞ የሚገኘው የሕዝብ መዝሙር (ብሔራዊ መዝሙር) እና የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ መዝሙር ያገኘችው 20ኛው ምዕት ዓመት ሲሆን በሦስት ሥርዓቶች ሦስት የተለያዩ መዝሙሮችን አስተናግዳለች፡፡ የመጀመሪያው መዝሙር በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (1923-1967) «ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ» የሚል መንደርደርያ ያለውና በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ግጥም ደራሲነት፣ በነርሲስ ናልባንዲያን ዜማ ቀማሪነት የተቀናበረው ነው፡፡ (የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን የሕይወት ታሪክና ሥነጽሑፋዊ ሥራ የጻፉት ዮሐንስ አድማሱ፣ የመዝሙሩ ግጥም ከዮፍታሔ ባለቅኔነትና ሌሎች ግጥሞቻቸው አኳያ እሳቸውን እንደማይገልጽና የሌላ ሰው ድርሰት ነው ብለዋል)፡፡

ሁለተኛው መዝሙር ሆኖ የመጣው ‹‹ኢትዮጵያ ቅደሚ›› የሚለው ሲሆን በኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ (1967-1979) ቀጥሎም በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (1980-1983) በአገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ብሔራዊ መዝሙር በአሰፋ ገብረማርያም ተሰማ ደራሲነት፣ በዳንኤል ዮሐንስ ዜማ ቀማሪነት አዲስ መዝሙር ቀርቦ እስከ 1983 .. ቆይቷል፡፡

1984 . ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ሲወጣ አዲሱን ሥርዓት የሚያንፀባርቅ አዲስ የሕዝብ መዝሙር በደረጀ መላኩ ገጣሚነት፣ በሰሎሞን ሉሉ ዜማ ደራሲነትወጣው «የዜግነት ክብር›› ይሰኛል፡፡

 የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር

በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ሰንደቅ ዓላማው የአከባበር ሥርዓት ነበረው፡፡ በመንግሥት ተቋማት በወታደራዊ ክፍሎችና በትምህርት ቤቶች የመስቀልና የማውረድ ሥርዓቱ ከሰንደቅ ዓላማ መዝሙር ጋር የተጣመረ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲወጣና ሲወርድ የክብር ሰላምታውን የደረሱት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ሲሆኑ ዜማውን ያወጡት አቶ እሸቴ መኰንን ናቸው፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ሲወጣ (ሲሰቀል) «ደሙን ያፈሰሰ ልቡ የነደደ›› የሚለው፣ ሲወርድ ደግሞ «ተጣማጅ አርበኛ›› ይዘመር ነበር፡፡

የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር ከዘውዳዊው ሥርዓት በኋላ አልቀጠለም፡፡  የሁለተኛው ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ አሰፋ ገብረማርያም ለሰንደቅ ዓላማው ማውጪያና ማውረጃ ግጥም ቢደርሱም ሶሻሊስት አገሮየባንዲራ መዝሙር የላቸውም በሚል ፈሊጥ ሥርዓት ሳይበጅለት እንደቀረ ይወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ