Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኦሊምፒክ ስፖርት ከ28 ወደ 33 ሊያድግ ነው

የኦሊምፒክ ስፖርት ከ28 ወደ 33 ሊያድግ ነው

ቀን:

– አበረታች ንጥረ ነገሮች የአይኦሲ ትልቁ አጀንዳ ሆኗል

31ኛው ኦሊምፒያድ እየተቃረበ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) 28 የነበረውን የኦሊምፒክ ስፖርት ወደ 33 ሊያሳድግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቲ አስታወቀ፡፡ የአበረታች ንጥረ ነገሮችን (ዶፒንግ) የመዋጋት ሥራ የአይኦሲ አንገብጋቢና ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ ሆኖ መቅረቡም ተነግሯል፡፡

በመጪው ክረምት በብራዚል በሪዮ ከተማ በሚካሄደው 31ኛው ኦሊምፒያድ ከ10,900 በላይ አትሌቶች፣ ከ21,100 በላይ ጋዜጠኞች፣ ከ7,000 በላይ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ተወካዮች፣ ከ3,200 በላይ ዳኞችና ተያያዥ ሙያተኞች እንዲሁም ከ20,000 በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ አባላትን እንደሚያሳትፍ በሪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ የቀረቡ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ረቡዕ ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጃፓን ቶኪዮ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ እ.ኤ.አ. በ2020 በሚካሄደው ቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅቱን አስመልክቶ አዳዲስ ውሳኔዎች ማስተላለፉ ተሰምቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ዳንኤል አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ አይኦሲ በነሐሴ ወር ሪዮ ዲጄኔሮ ላይ በሚያደርገው 129ኛው መደበኛ ስብሰባው፣ 28 የነበሩትን ስፖርቶች አምስት በመጨመር ወደ 33 ከፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ምክረ ሐሳብ (ፕሮፖዛል) በቶኪዮ ስብሰባው ተቀብሎታል፡፡ ውሳኔው በኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያውና ለዘመናዊው ኦሊምፒክ ትልቅ እመርታ ስለመሆኑም ተመልክቷል፡፡

እንደ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያው፣ በ2020 የኦሊምፒክ ፕሮግራም ውስጥ ይካተታሉ የተባሉት አምስቱ ስፖርቶች ካራቴ፣ የመንሸራተቻ ላይ ስፖርት (ስኬት ቦርዲንግ)፣ የተራራ ላይ መውጣት (ስፖርት ክላይምቢንግ)፣ የማዕበል ቀዘፋ (ሰርፊንግ)፣ እንዲሁም በአሜሪካና በካናዳ ሕዝቦች ዘንድ በስፋት የሚዘወተሩት ቤዝ ቦልና ሶፍት ቦል ናቸው፡፡ ስፖርቶቹ የሚዘወተሩት በቡድንና በነጠላ፣ በቤት ውስጥና ከቤት ውጪ የሚደረጉ ውድድሮችን አካተው የሚይዙ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ ስፖርቶቹ የኦሊምፒክ ስፖርት ተብለው እንዲካተቱ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክረ ሐሳብ መሆኑንም አክለዋል፡፡ በአምስቱ ስፖርቶች በድምሩ 474 አትሌቶች እንደሚሳተፉም ታውቋል፡፡

 በሌላ በኩል በዚህ ወቅት ከማናቸውም ጊዜ በበለጠ ለ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ ንፁህ አትሌቶችን ለመጠበቅ ሲባል የአበረታች ንጥረ ነገሮችን የመዋጋት ሥራ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አንገብጋቢና ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳው እንደሆነ ታውቋል፡፡ እንደ አቶ ዳንኤል መግለጫ ከሆነ፣ የአበረታች ንጥረ ነገሮችን ምርት የተጠቀመ፣ ያስጠቀመ፣ ያቀረበ፣ ያመቻቸ ማንኛውም አካል፣ ባለሥልጣን፣ አሠልጣኝና አትሌት ቅጣቱ ከባድ ይሆናል፡፡ ለዚህ ፈታኝና የስፖርቱ ጠላት ለሆነው ዕፅ የሚከተለው ፖሊሲ ዜሮ መሆኑንም ጭምር ይፋ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

አይኦሲ ለዚህ ፕሮግራም ቅድመ ምርመራ የያዘው በጀት ካለፉት ዓመታት በሁለት እጥፍ ያደገ መሆኑ፣ ለዚህም ሲባል ከሪዮ 2016 ኦሊምፒክ አስቀድሞ የሚደረገው የዶፒንግ ምርመራ ፕሮግራም በዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖችና ከአገር አቀፍ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ድርድቶች ጋር በጋራ የሚሠራ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡ ይኼ ፕሮግራም በዋናነትም ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም ተግባራዊ ባላደረጉ አገሮች ማለትም ኬንያ፣ ሩሲያና ሜክሲኮን አጥብቆ የሚመለከት መሆኑም ታውቋል፡፡   

የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች በቅርቡ በኢትዮጵያ ከተቋቋመው ብሔራዊ የሥነ ምግባር ኮሚሽን ጋር በተለይ ሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታ ላይ እንዳይሳተፉ ለጊዜው የታገዱ አትሌቶችን ጉዳይ አጢኖ ፈጣን የውሳኔ ሐሳብ እንዲሰጥ ስለመጠየቁም ተብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...