Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን አቋቁማለሁ አለ

  የአዲስ አበባ አስተዳደር ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን አቋቁማለሁ አለ

  ቀን:

  – በቅርቡ ኤጀንሲ ይቋቋማል

  በልማት ምክንያት ከነባር ቀዬአቸው በመፈናቀላቸው ለችግር የተጋለጡ አርሶ አደሮች በድጋሚ እንደሚያቋቁም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ አስተዳደሩ ከዚህ በኋላም ቢሆን በልማት ምክንያት ለሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች፣ በቂ ካሳ ተከፍሏቸው ከከተማው ልማት ተጠቃሚ እንደሚደረጉ አመልክቷል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. የካቢኔያቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ለምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ከዚህ ቀደም በልማት ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን በድጋሚ የሚያቋቁም ኤጀንሲ ይመሠረታል፡፡

  ከንቲባ ድሪባ እንዳሉት፣ የካፒታሊስት ሥርዓት እስካለ ድረስ ከተማ መስፋፋቱ የግድ በመሆኑ በከተማ ኢንዱስትሪና ኢቨስትመንት ሲስፋፋ አርሶ አደሮች መፈናቀላቸው አይቀርም፡፡

  ‹‹ዋናው ነገር አርሶ አደሮች መነሳታቸው አይደለም፡፡ ዋናው ቁም ነገር ከቦታቸው የሚነሱ አርሶ አደሮች በቂ ካሳ እንዲያገኙና በከተማ ልማቱ የሚጠቀሙ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፤›› በማለት የካቢኔያቸውን አቋም አስረድተዋል፡፡

  ከንቲባው ጨምረው እንዳብራሩት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በጋራ እየሠራ ነው፡፡ መንግሥት ለአርሶ አደሮች በቂ ካሳ የሚከፈልበትን አሠራር ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ ወስዶ እያጠና እንደሆነ የጠቆሙት ከንቲባው፣ አርሶ አደሮች በከተማ ውስጥ መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸውና በዘመናዊ የእርሻ ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ የሚቻልበት መንገድ እየተቀየሰ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

  ከሁለት አሥርት ወዲህ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ጎን እየተለጠጠች የምትገኘው አዲስ አበባ፣ ነባር አርሶ አደሮችን በማፈናቀል በምትኩ የመኖሪያ ቤትና የኢንዱስትሪ ልማት እየተካች ትገኛለች፡፡

  በዚህ ሒደት አስተዳደሩ የሚያቀርበው የካሳ ክፍያ፣ ምትክ ቦታ፣ ለጊዜያዊና ለነባር ምርቶች የሚሰጠው ካሳ አነስተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደሮች እንደሚገልጹ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በርካታ አርሶ አደሮች ለችግር የተጋለጡ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ በልማቱ መስፋፋት ምክንያት መፈናቀል እንደማይቀርላቸው የተረዱ አርሶ አደሮችም ሥጋታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

  አርሶ አደሮችን የማቋቋም ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ማኅበራዊ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው በወቅቱ እንደገለጹት፣ ለማኅበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጠው የቆዩ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም የሚያስችለው ጥናት ተጠናቋል፡፡

  ጥናቱ ከአርሶ አደሮች ጋር ምክክር የተደረገበት መሆኑንና የማቋቋም ሥራውን ማካሄድ የሚያስችለው የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን አቶ ኤፍሬም ገልጸው፣ በቅርቡ ሰነዱ ለካቢኔ እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡

  በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለወራት የዘለቀው ተቃውሞ ዋነኛ መነሻ ለአርሶ አደሮች የሚሰጠው ካሳ መጠን ፍትሐዊ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይታወሳል፡፡   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ኢዜማ በምሥራቅ ወለጋ ዞን የንፁኃን ጭፍጨፋ አሳስቦኛል አለ

  በግጭት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎች ራሳቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ መታጠቅ...

  ኦሲፒ አፍሪካ ጨዋማ መሬት ለማከም የሚረዳ ምርምር ይፋ አደረገ

  በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለአርሶ አደሩ የሚሠራጨውን የአፈር ማዳበሪያ በማቅረብ...

  የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በየዓመቱ አርባ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን እያስተዋወቀ መሆኑን ገለጸ

  የአገሪቱን የግብርና ልማት በምርምር የሚያግዙ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማልማት፣ የግብርና...

  የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በአክሲዮን ለመደራጀት የሚያስፈልጋቸውን የተሽከርካሪ ብዛት የሚወስን መመርያ ተረቀቀ

  የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ባለንብረቶች ከማኅበርነት ወጥተው አክሲዮን ሲቋቋሙ፣ ከሚጠበቅባቸው...