Saturday, January 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልድምፃዊ ጊታሪስትና መምህር መስፍን አበበ (1944 - 2008)

ድምፃዊ ጊታሪስትና መምህር መስፍን አበበ (1944 – 2008)

ቀን:

በብዙዎች ዘንድ በተለይ የሚታወቀው ቦክስ ጊታሩን ይዞ ለየት ባለው ቅላፄው በሚጫወታቸው ዘፈኖቹ ነው፡፡ ድምፃዊው መስፍን አበበ፡፡ የሙዚቃ መሣሪያ እየተጫወቱ ከሚያቀነቅኑ ግንባር ቀደምት መካከል ቀድሞ ለታዳሚ የሚመጣው መስፍን ነው፡፡

‹‹ያዢልኝ ቀጠሮ ቦታ ምረጪና

ወይ ሐረር ወይ ሸገር አጫውቺኝ ነይና›› እያለ ከምድር ባቡር ጋር አስተሳስሮ በሚጫወተው ዜማው እንዲሁም ‹‹አይሽ አይሽና ይመጣል እንባዬ››፣ ‹‹እንዲያው ጉም ጉም››፣ ‹‹መልካም ልደት›› ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በደሴ ወይዘሮ ስሂን ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ ጋር በመሆንና ሙዚቃ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጫወት ወደ ጥበቡ የዘለቀው ድምፃዊና ጊታሪስት መስፍን፣ በተለያዩ ሙዚቃ ቤቶች 22 ካሴቶች ማሳተሙ ይነገርለታል፡፡

መስፍን ሕይወቱን ‹‹የመንፈስ አረቄ የነፍስ እህል ውኃ›› እየተባለች ከሚነገርላት ሙዚቃ ጋር ብቻ አላቆራኘም፡፡ የአድማጮችን ኅሊና የሚኮረኩሩ ብሂልን ከባህል ያዛመዱ፣ ነውን ከነበር የሚያጣቅሱ ሥራዎቹን በሙዚቃው ብቻ ማስተላለፍ አልተወሰነም፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ትውልድን ለማነፅ እንደ አባቶቹ አርዓያነት ያለውን የአስተማሪነት ሙያን በመፍቀድና ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመዝለቅ ሙያውን ጨብጧል፡፡ ሲያስተምር፣ ሲያዜም፣ ጊታር ሲጫወት ኖሯል፡፡

አስተማሪነቱ የቀለም ትምህርት ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመኑ ወጣት ከነበሩ አሁን አንጋፋ ድምፃውያን ዕውቀቱን አልነፈጋቸውም፡፡ አንዱ ማሳያ የታዋቂው ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ምስክርነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ድረ ገጽ ላይ እንደተመለከተው፣ ‹‹ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ዜማዎችን ሲፈጥር በፉጨትና በእንጉርጉሮ ሲሆን፣ ከአንድ ወቅት በኋላ በቦክስ ጊታር እየተጫወተ የሚያቀነቅነውን ዝነኛ ድምፃዊ መስፍን አበበ ለሥራ ወላይታ በመጣ ጊዜ የማግኘት ዕድሉ አጋጥሞት፣ ለዜማ መለማመጃ የቦክስ ጊታር አጨዋወት እንዳስተማረው ይታወቃል፡፡››

ከአባቱ አቶ አበበ ወልደ ማርያምና ከእናቱ ከወ/ሮ ወይንሸት ተሾመ በ1944 ዓ.ም. የተወለደው መስፍን አበበ፣ በአሥራዎቹ ዓመታት በተማረው ሙያ በድምፃዊነትና በሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነቱ እንዲሁም በመምህርነቱ ይታወሳል፡፡

ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በ64 ዓመቱ ያረፈው ድምፃዊና መምህር መስፍን፣ ሥርዓተ ቀብሩ በማግስቱ በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እኩለ ቀን ላይ ተፈጽሟል፡፡

ድምፃዊ፣ ሙዚቀኛና መምህር መስፍን ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...