Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየሥነ ጽሑፍ ሐያሲው አብደላ እዝራ ስንብት (1950-2008 ዓ.ም.)

  የሥነ ጽሑፍ ሐያሲው አብደላ እዝራ ስንብት (1950-2008 ዓ.ም.)

  ቀን:

  አዳዲስ መጻሕፍት ታትመው ለንባብ ከበቁ በኋላም ሆነ ከመውጣታቸው በፊት በሚሰነዝሩት አስተያየቶች ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው ሐያስያን አንዱ አብደላ እዝራ ነው፡፡ የተለያዩ የመጻሕፍት ምርቃቶች እንዲሁም መጻሕፍት ላይ ያተኰሩ የውይይት መርሐ ግብሮች ሲካሄዱ ተገኝቶ ጥልቅ ሥነ ጽሑፋዊ ምልከታዎቹን አቅርቧል፡፡ የሰሉ ሒሶችን በተለያዩ ጋዜጣዎችና መጽሔቶች ላይም ለንባብ አብቅቷል፡፡

  በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ሐያስያን ያላቸው ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ጽሑፎች ላይ የሚያቀርቡት ሒስ ተቺ፣ አሞጋሽ፣ ገንቢ፣ አስተማሪና አራቂም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ስማቸው ከሚጠራ ሐያስያን መካከል አንዱ የሆነው አብደላም ለዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

  ይህ ሐያሲ ከግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ባደረበት ሕመም ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ ግንቦት 27 ቀን ከቀኑ በ10፡30 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ድንገተኛ የሆነው የሐያሲው ሕልፈት የሥነ ጽሑፍ ቤተሰቦችንና ወዳጅ ዘመዶቹንም ያስደነገጠ ነበር፡፡ ግንቦት 28 ቀን ሥርዓተ ቀብሩ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመ ሲሆን፣ ቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ የመጨረሻ ስንብታቸውን አድርገዋል፡፡

  አዲስ አበባ፣ መርካቶ አንዋር መስጊድ አካባቢ ከአባቱ ከአቶ መሐመድ ሳልህ አልአረግስኢና ከእናቱ ወ/ሮ መሪሃም በ1950 ዓ.ም. የተወለደው አብደላ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል በአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍልን በልዑል ወሰን ሰገድ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በተፈሪ መኰንን ተምሯል፡፡

  ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደ የመን፣ ሠንዓ ተጉዞ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን አጠናቋል፡፡ እዛው የመን ውስጥ በየመኒ ኤርዌይስ ተቀጥሮ ጡረታ እስከወጣበት ጊዜ በመሥሪያ ቤቱ ሠርቷል፡፡ አብደላ አብዛኛውን የሕይወቱን ጊዜ በሥነጽሑፍ ሥራዎች ላይ ምርምር አያደረገ ቆይቷል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ የበርካታ ገጣምያንና ደራስያን ሥራዎች ላይ ትንታኔዎች አቅርቧል፡፡

  በአዲስ ዘመንና አዲስ አድማስ ጋዜጦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) በሚያዘጋጀው ብሌን መጽሔት ላይ ትንታኔዎቹ ቀርበዋል፡፡ የበርካታ አንጋፋና ወጣት ደራስያን ሥራዎችን በሰላ ብዕሩ ዳሷል፡፡ በጽሑፋቸው ላይ ትንተና ከሰጠባቸው ደራስያን መካከል በዓሉ ግርማ፣ አበራ ለማ፣ ደበበ ሰይፉ፣ ሲሳይ ንጉሡ፣ አዳም ረታ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ነብይ መኰንን፣ ዓለማየሁ ገላጋይ፣ ኤፍሬም ሥዩም፣ ደምሰው መርሻና በድሉ ዋቅጅራ ይጠቀሳሉ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...