Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጋምቤላ ማረሚያ ቤትና በተለያዩ ቦታዎች የአኝዋ ተወላጆችን በመግደል የተጠረጠሩ 45 ግለሰቦች ተከሰሱ

በጋምቤላ ማረሚያ ቤትና በተለያዩ ቦታዎች የአኝዋ ተወላጆችን በመግደል የተጠረጠሩ 45 ግለሰቦች ተከሰሱ

ቀን:

ካልተያዙ ከ100 በላይ ከሚሆኑ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በጥር ወር 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ፖሊስ ሆነው ተመድበው የሚሠሩና ታራሚ የነበሩ፣ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ታስረው የነበሩ የአኝዋ ተወላጆችን በግፍ ደብድበው፣ በሥለት ወግተውና በመሣሪያ ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩ 45 ግለሰቦች ተከሰሱ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው 45 ተከሳሾች አብዛኛዎቹ የኑዌር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በማረሚያ ቤቱ የተመደቡ የአኝዋ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ፖሊሶችን ትጥቅ ካስፈቱ በኋላ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ላሉት የኑዌር ተወላጆች ዱላ፣ ሥለትና ድንጋይ በመስጠት የአኙዋ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ድብደባ በማድረስ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲሞቱ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በዓቃቤ ሕግ የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በታራሚዎቹ ላይ ብቻ ሳይሆን በክልሉ ጅሀር ወረዳ ለሥራ ሄደው ወደ ጋምቤላ ከተማ እየተመለሱ የነበሩትን የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጋዴድ ጎኝን ከመኪና አስወርደው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሏቸው ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ በርካታ የአኝዋ ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየመረጡ በመግደላቸው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለን)፣ 35፣ 38 እና 539 (1ሀ)ን መተላለፋቸውንና በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ እንደቀረበባቸው ለፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ ሰነድ ያስረዳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተከሳሾቹ ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ በራሳቸው አቅም ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመግለጻቸው፣ ፍርድ ቤቱ ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው ለተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...