Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅ‹‹አህያ ረግጦኝ ነው ልጄ››

‹‹አህያ ረግጦኝ ነው ልጄ››

ቀን:

አንዲት አጠር፣ ደልደል ያለች ደባካ መሳይ የአለቃ ገብረሐና ጎረቤት፣ ‹‹አባ ሰው ሁሉ ድንቼ፤ የኔ ድንች እያለ ያቆላምጠኛል›› ብትላቸው፣ ‹‹አዬ ሞኝት፣ እውነት መስሎሽ ነው? ድንቼ፤ ድንቼ የሚሉሽ ሊልጡሽ እንጂ ነው አሉዋት፡፡›› […] ድንቡሼዋ ጐረቤታቸው አዲስ ልብስዋን ልታስመርቅ እየሮጠች ወደቤታቸው ስትመጣ አመለጣትና መአዛው ቤቱን አወደው፡፡ አባ ገብረሐና ግን እንዳላወቀ ሰው ‹‹በውኃ ይለቅልሽ፤ ጥሎሽ ይሂድ›› ብለው ከመረቋት በኋላ ‹‹እንግዲህ ይህችን ከሰው ዘንድ ስትደርሽ ብን እያደረግሽ ኩሪ›› ብለው አሰናበቷት፡፡

ድንቡሼም ለአቅመ ሔዋን እንደደረሰች አንድ አህያ ነጂ አገባች፡፡ ታዲያ ገብረሐና ይንቁት ኖሮ አንድ ቀን ሰውየው አህዮች እየነዳ ባጠገባቸው ሲያልፍ፤ ‹‹ጤና ይስጥልኝ አባ›› ብሎ የግዜር ሰላምታ ቢያቀርብላቸው፤ ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን፤ እንደምን ዋላችሁ?›› በማለት መለሱለት፡፡ አህያ ነጂውም በዚህ ተበሳጭቶ ስለነበር ቤታቸው እስኪገቡ ጠብቆ ገላጋይ በሌለበት ቀጠቀጣቸው፡፡ ዱላው ክፉኛ ጐድቷቸው ስለነበርም ታመው ተኙ፡፡ አመሻሹ ላይ እያነከሱ ከውጭ ሲመለሱ አህያ ነጂው ድንቡሼን አስከትሎ እንዳላወቀ ሰው ሊጠይቃቸው መጣ፡፡ ‹‹አባ ምን ሆኑ?›› ሲልም ጠየቃቸው፡፡ ‹‹አህያ ረግጦኝ ነው ልጄ›› አሉት ፈጠን ብለው፡፡

  • አረፈዓይኔ ሐጎስ ‹‹አለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸው››
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...