Wednesday, June 12, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የርብ መስኖ ግድብ ከአሥር ዓመታት በኋላ ተጠናቀቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በ2000 ዓ.ም. የተጀመረው የርብ መስኖ ልማት ግድብ፣ ከአሥር ዓመታት በኋላ ግንባታው ተጠናቆ እሑድ ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ ሊመረቅ ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በ2000 ዓ.ም. በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ ግንባታው በተለያዩ ችግሮች ለስድስት ዓመታት ዘግይቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በ1.6 ቢሊዮን ብር በጀት የተጀመረ ቢሆንም ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ፣ በጀቱ እስካለፈው ዓመት ጥቅምት 2010 ዓ.ም. ድረስ 3.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡

የግድቡን ዲዛይንና የቁጥጥር ሥራውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ሲሆን፣ ግንባታውን ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አከናውኖታል፡፡

ሃያ ሺሕ ሔክታር መሬት ማልማት ያስችላል የተባለው ይህ የርብ መስኖ ልማት ግድብ የዘገየው በዲዛይን ለውጥ፣ በኮንትራክተሩና በአማካሪ ድርጅቱ አቅም ውስንነትና የልምድ ማነስ፣ በውኃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስተዳደር ችግርና በግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት እጥረት ምክንያት መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ግንባታው በመጠናቀቁ በሚቀጥለው ሳምንት የፌዴራልና የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ይመረቃል ተብሎ መርሐ ግብር ተይዟል፡፡

በኢትዮጵያ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በየጊዜው ቢጀመሩም በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እየተጠናቀቁ ስላልሆኑ፣ አገሪቱን ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት ላይ ናቸው፡፡

የብሔራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን እነዚህን ችግሮች ለመፍታትና ከዚህ በኋላም የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች በሥሩ እንዲያልፉ ራሱን የቻለ ዳይሬክቶሬት አቋቁሟል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ አዳዲስ የሚጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሁለንተናዊ ዕቅድ ገምግሞ ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ እየተጓተቱ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ መላ ይዘይዳል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች