Monday, June 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኤርባስ ኩባንያ በአዲስ አበባ ለዕይታ ያቀረበው ሔሊኮፕተር ተፈላጊነት ማትረፉ ተገለጸ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በዓለም ትልቅ የገበያ አድማስ ከዘረጉ ግዙፍ አውሮፕላን አምራቾች አንዱ የሆነው ኤርባስ ኩባንያ ኤች125 የተሰኘውን ሔሊኮፕተር በአዲስ አበባ እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ዓርብ ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው የማሳያ በረራ ጋዜጠኞችንና ሌሎችም አካላትን በመጋበዝ አዲስ አበባን አስጎብኝቷል፡፡

የኩባንያው ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ ያልጠበቁት ከፍተኛ ፍላጎት ከመንግሥት ባሻገር በግሉ ዘርፍ በኩልም በማየታቸው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሔሊኮፕተሩን ለማቅረብ የሚያስችል ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡

ከወታደራዊ ተልዕኮዎች ባሻገር ለሲቪል አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ የሔሊኮፕተር ሥሪቶች ያሉት ኤርባስ፣ ኤች125 ሔሊኮፕተር ባለው ከፍተኛ ብቃት ሌሎች በተመሳሳይ ደረጃ ከተፈበረኩ ሔሊኮፕተሮች ብልጫ እንዳለውና በቀንና በሌሊት በሚካሄዱ በረራዎችም ብቃቱን እንዳስመሰከረ ስለሔሊኮፕተሩ የቀረቡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ለነፍስ አድን ፍለጋዎች፣ ለእሳት አደጋ፣ ወንጀለኞችን ለማደን በሚደረጉ ቅኝቶችና በሌሎችም ፈርጀ ብዙ ኦፕሬሽን መስኮች አገልግሎት የሚሰጠው ኤች125 ሔሊኮፕተር፣ በነዳጅ ቆጣቢነቱም ተመራጭ እንደሆነ ተወስቷል፡፡ ከአብራሪው በተጨማሪ እስከ ስድስት ሰዎች ማሳፈር እንዲችል ተደርጎ የተፈበረከ ነው፡፡ ዘና ብለው የሚጓዙ ተሳፋሪዎችን እንዲጭን ካስፈለገ ግን ከአብራሪው በተጨማሪ አራት ተሳፋሪዎችን ማጓጓዝ የሚችል ፈጣን ሔሊኮፕተር ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር እስከ 2,800 ኪሎ ግራም የሚመዝን ጭነትም የማጓጓዝ አቅም እንዳለው ተነግሮለታል፡፡

በዋጋ ደረጃ አዲሱ ኤርባስ ኤች125 እስከ 2.9 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ እንደሚችል ሲታወቅ፣ ያገለገለው ከ2.2 እስከ 2.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ይገመታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች