2 የበግ ምላስ – የበሬ አንድ
3 ቁንዶ በርበሬ ያልተፈጨ
6 ቀረፋ ያልተፈጨ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የሾርባ ማንኪያ ኮምጣጤ
አሠራር
- ምላሱን ፍም ላይ አስቀምጦ አምስት ደቂቃ ማቆየትና መላጥ፡፡
- የተላጠውን ምላስ ንጹህ ውኃ ላይ መጣድና እስኪበስል ድረስ መቀቀል፡፡
- ቁንዶ በርበሬ፣ ቀረፋ፣ ጨውና ኮምጣጤ ጨምሮ ማንተክተክ፡፡
- ሲበስል ማውጣት፡፡
- በተፈለገው ፎርም ቆርጦና አሳምሮ ማቅረብ፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚኣኬል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)