Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለእጅ ኳስ ስፖርት ዕድገት ዘመናዊና ስትራቴጂካዊ አመራር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ለእጅ ኳስ ስፖርት ዕድገት ዘመናዊና ስትራቴጂካዊ አመራር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ቀን:

በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ጨዋታ መሆኑንና የዕድሜውን ያህል ላለማደጉ የአመራር ችግር ዋነኛ ተጠያቂ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ፍትሕ ወልደ ሰንበት ይህን የተናገሩ ሦስተኛው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሐዋሳ በተካሄደበት ወቅት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ በፌዴሬሽን ደረጃ የተቋቋመው በ1962 ዓ.ም. ነው፡፡

አቶ ፍትሕ ወልደ ሰንበት የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ለስፖርቱ ወደኋላ መቅረት በርካታ ምክንያቶችን ጠቅሰዋል፡፡ የእጅ ኳስ ጨዋታ እንደ ውድድር ሲቋቋም በሦስት ወታደራዊ ተቋሞች ብቻ ሲካሄድ መቆየቱንና ተቋማቱም ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ ፖሊስና መከላከያ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ አቶ ፍትሕ  ስፖርቱ በዛን ጊዜ በጣም ብዙ ተመልካች የሚከታተሉትና ጥሩም መዝናኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ከዛ በኋላ ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ ራሱን ችሎ የሊግ ውድድር አድርጎ እንደማያውቅ ነው ያስረዱት፡፡ ይህም ለዕድገቱ መጓተት ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው ብለዋል፡፡ የገንዘብም ችግር እንዳለ ሆኖ ዋናው ግን የአስተዳደር ችግር እንደሆነ በአጽንኦት የገለጹት፡፡ በቂ ጊዜ ሰጥቶ አለመሥራት ስፖርቱ ታዋቂ እንዲሁም አዝናኝ እንዳይሆን አድርጎታል ሲሉ ነው ያከሉት፡፡

አሁን ምን እየተሠራ እንደሆነ አቶ ፍትህ ሲገልጹ፣ ‹‹መጀመርያ ያደረግነው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ውስጥ መምጣት አለበት በሚል የዘንድሮውን ፕሪሚየር ሊግ ማነቃቂያ አድርገነዋል፡፡ ያሉትን ሦስት ክለቦች ይዞ ፕሪሚየር ሊግ ማድረግ ስለማይቻል ሁሉንም ክልሎች እናሳትፍ በሚል የዘንድሮውን ለማስተዋወቅ ያህል አራት ክልሎችን መርጠናል፤›› ብለዋል፡፡ ክልሎቹ ሐዋሳ፣ ባህርዳር፣ ድሬዳዋና ትግራይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ውድድሩንም አዲስ አበባ ላይ በማድረግ ወደ ኅብረተሰቡ ለማስረፅ ተወስኖ እየተሠራ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ አማራ ክልል ለሚቀጥለው እንደሚያዘጋጅ መግለጹን ያስታወቁት፡፡ አቶ ፍትሕ ‹‹ቀሪዎቹን ይዘን አሁን ሐዋሳ ላይ እያካሄድን እንገኛለን፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ፍትሕ ሌላው ትልቁ ስኬት እንደሆነ የገለጹት ፌዴሬሽኑ የዓለም የእጅ ኳስ ፌዴሬሽንና የአፍሪካ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የነበረውን ግንኙነት እንደ አዲስ በመቀጠላቸው ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አገር ውስጥ እንዲካሄዱ በማድረግ ስፖርቱ እንዲያንሰራራ ስለመደረጉም ተናግረዋል፡፡ ‹‹የዓለም እጅ ኳስ ፌዴሬሽን በነፃ የሚያዘጋጀውን ውድድር ተጠቅመንበታል፡፡ በዚህም በእጅ ኳስ የኢትዮጵያ ስም እንዲጠራ ሆኗል፡፡ በመጨረሻም የገንዘብ አቅማችንን ለመፍታት ደግሞ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሥራት እጅ ኳሱን በክለቦች እንዲታቀፍ በማድረግ የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ እያዘጋጀን የገቢ ችግሮችን እንቀርፋለን፤›› ብለዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ትንሿንና ትልቁን ስታዲየም በመጠቀም ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ከተፈቀደላቸው አምስት ፌዴሬሽኖች አንዱ እጅ ኳስ ስለሆነ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በገቢም በአመራርም ራሱን ችሎ እንደ እግር ኳሱ ሕዝቡ ውስጥ ተወዳጅ እንዲሆን እንደሚሠሩም ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮው ሦስተኛው የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ የወንዶች ውድድር ከመጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 6 በሐዋሳ እየተካሄደ ሲሆን ፌዴራል ፖሊስ፣ መከላከያ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ቡታጅራ ከተማ፣ ሐድያ ከተማ፣ ከንባታ ዱራሜ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ በማጣሪያ ጨዋታ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ለዋንጫ ደርሰዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...