Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በሐሰተኛ ሰነድ የግንባታ ብረት አስገብተው መንግሥትን 13.6 ሚሊዮን ብር በማሳጣት የተጠረጠሩ ተከሰሱ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስለው በመሥራት የባለአምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ ኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣትና ለኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰጠውን የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም የግንባታ አርማታ ብረት ያለ ቀረጥ በማስገባትና ለሌላ አካል በመሸጥ በመንግሥት ላይ በድምሩ ከ13.6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ካወጡ በኋላ የነፃ መብት ለማግኘት ማሟላት ከሚገባቸው ሰነዶች መካከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ የሚሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫና የግንባታ ፍቃድ የምስክር ወረቀት አስመስለው የሠሩት አቶ አሰፋ ሙሄ ዓሊ የተባሉ ተጠርጣሪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል፡፡

ተጠርጣሪው እውነተኛ አስመስለው ያዘጋጁትን ሐሰተኛ ሰነድ ለአዲስ አበባ ወጪና ሌሎች ዕቃዎች ማስተናገጃ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የግብርና ሶሻል ዘርፎች ቡድን በማስገባት ግምቱ 6.2 ሚሊዮን ብር የሆነ 987.865 ሜትሪክ ቶን የግንባታ አርማታ ብረት ምንም ዓይነት ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር ውስጥ ማስገባታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ በመሆኑም ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈል የሚያደርግ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በሕዝብና መንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አክሏል፡፡ ዳውድ ሰይድ ዳምጠው የተባሉት ተጠርጣሪ የአቶ አሰፋ አስፈጻሚ በመሆን ከፍተኛ ትብብር ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡

አቶ እዮብ ወርቅነህ የተባሉት ተጠርጣሪ ከላይ ለተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ለሆቴል ግንባታ የሚሆን የግንባታ ዕቃዎች ስፍር ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀማቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ አቶ አሰፋ የንግድ ትርፍ ግብር አለመክፈላቸውንና መንግሥት ሊያገኝ ይገባ የነበረውን 1,227,108 ብር እንዲያጣ ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

ተከሳሾቹ በሆቴል የኢንቨስትመንት አገልግሎት ንግድ ሥራ ፍቃድ በመጠቀም ወደ አገር ውስጥ ያስገቡትን 987.865 ሜትሪክ ቶን የግንባታ አርማታ ብረት ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ሲያስተላልፉ፣ ግብር ለመሰወር በማሰብ በግብሩ ዘመን መክፈል የነበረባቸውን ተጨማሪ እሴት ታክስ 6,144,855 ብር አለመክፈላቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡

ታምራት አቡ፣ ኢሳቅ ፀጋዬና ስመኝ ግርማ የተባሉት ተጠርጣሪዎች የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ሲሆኑ፣ ከላይ የተጠቀሱት ተከሳሾችን በተለያየ መንገድ በመርዳት በተለይ አሰፋ ሙሄንና ዳውድ ሰይድን ለመጥቀም በማሰብ የግንባታ አርማታ ብረት ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ በማድረግና ዲክላራሲዮን በመበተን ሥልጣናቸውን አላግባብ የመጠቀም ወንጀል መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ ጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች