ለአምስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት ሙላቱ ተሾመን (ዶ/ር) የተኩት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ሹመታቸውን በቃለ መሃላ ተቀብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አራተኛ ከሴቶች የመጀመርያዋ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ልዩ ስብሰባ ነው የፕሬዚዳንትነት መንበሩን የተረከቡት፡፡ ፎቶዎቹ የአዲሷን ፕሬዚዳንት ሥርዓተ ሲመት፣ የቀድሞውን ሽኝት ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡