Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርት‹‹ትልቁ ህልሜ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ነበር ያንን አሳክቻለሁ››

  ‹‹ትልቁ ህልሜ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ነበር ያንን አሳክቻለሁ››

  ቀን:

  ፅጋቡ ገብረማርያም፣ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የኦሊምፒክ ተወዳዳሪ

  በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የኦሊምፒክ ጨዋታ በክረምቱ በደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ ከተማ ላይ ይከናወናል፡፡ በዝግጅቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ200 በላይ አገሮች የተወጣጡ 10,000 አትሌቶች እንደሚሳተፉ የሪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ በአትሌቲክስ፣ በብስክሌትና በውኃ ዋና መሳተፏን ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ ዝግጅቷን አጠናክራ መቀጠሏ እየተነገረ ይገኛል፡፡

  ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በ31ኛው ኦሊምፒያድ አገሪቱን በብቸኝነት ለሚወክለው ብስክሌተኛ ፅጋቡ ገብረማርያም እያደረገ ያለውን ድጋፍና ክትትል አስመልክቶ ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

  ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በ1949 ዓ.ም. በአውስትራሊያ ሜልቦርን ኦሊምፒክ በብስክሌት ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ ከወከሉት ብስክሌተኞች አንዱ የነበሩትን ገረመው ደንቦባን በመግለጫው በመጋበዝ፣ ለብቸኛው የሪዮ ኦሊምፒክ ተወካይ ፅጋቡ ገብረማርያም የካበተ ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉት አድርጓል፡፡ አትሌቱ በበኩሉ በብስክሌት በቀደምትነታቸው ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ግንዛቤና እገዛ ባልነበረበት በዚያን ወቅት ለኦሊምፒክ ተሳትፎ ከበቁት ታላቁ ገረመው ደንቦባ ጋር መገናኘቱ ከምንም በላይ እንደሚያስደስተው ገልጾ አደራው በተሳትፎ ብቻ ሳይሆን በውጤት ለማጠናቀቅ ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡

  የቀድሞው ብስክሌተኛ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋቸው፣ በግል ጥረት ካልሆነ እንዲህ እንዳሁኑ የተመቻቸ ነገር ካለመኖሩ ባሻገር፣ የሜልቦርን ኦሊምፒክ ዕድሉን እንኳ ለማግኘት ንጉሡን በአካል አግኝተው ካነጋገሩ በኋላ የተፈጠረላቸው አጋጣሚ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ፅጋቡ ገብረማርያምን የመሰሉ ወጣቶች መገኘታቸው በሕይወታቸው አንድ ነገር እንደጨመረላቸው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

  አንጋፋው ብስክሌተኛ ትውስታቸውን ሲቀጥሉ፣ እሳቸው የካበተ ልምድና ተሞክሮ ቢኖራቸውም አገራቸውን ማገልገል የሚገባቸውን ያህል ለማገልገል ዕድል እንዳልተመቻቸላቸውም ተናግረዋል፡፡ ‹‹በእኔ እምነት ምክንያቱ ለምን እንደሆነ እስካሁን  ምንም የተገለጸልኝ ነገር የለም፡፡ ይህን እውነታ የምናገረው የቀድሞውን ሥርዓት ለማጣጣል አይደለም፡፡ በወቅቱ የነበርን ሁሉ ስፖርተኛ ለመሆን የበቃነው በፈጣሪና በራሳችን የግል ጥረት ብቻ ነበር፤›› ብለው፣ በጊዜው ከነበረው አንፃር አሁን የተሻለ ስለመሆኑ ነው ያስረዱት፡፡ ቀጥለውም የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዓርማን ለፅጋቡ ገብረማርያም አስረክበዋል፡፡

  ‹‹ትልቁ ህልሜ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ነበርና ያንን አሳክቻለሁ፡፡ ይኼ በሕይወቴ የምሰጠው ትልቁ ቦታ ነው፤›› በማለት አደራውን የተረከበው ፅጋቡ የሪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎው በውጤት የታጀበ ይሆን ዘንድ ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡ በብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውም ለአትሌቱ ዝግጅት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት ስለመሆኑም ተናግሯል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...