Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹ደም ያስተሳስረናል››

‹‹ደም ያስተሳስረናል››

ቀን:

የዓለም የጤና ድርጅት በየዓመቱ ጁን 14 (ሰኔ 7) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የዓለም ደም ለጋሽ ቀን ምክንያት በማድረግ አስተማማኝ የጤናማ ደም አቅርቦት እንዲኖር ከዓለም አገሮች ከፊል ያህሉ የበጐ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ እንዲጨምር ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

የዘንድሮ የዓለም ደም ለጋሽ ቀን ‹‹ደም ያስተሳስረናል›› በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ መሪ ቃሉ ሰዎች በፍቃደኝነት ደም በመለገስ የሌሎች ብዙዎችን ሕይወት እንዲታደጉ ሊያነሳሳ እንደሚችልም ታምኗል፡፡

‹‹ደም ያስተሳስረናል›› በሚል ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የበጐ ፈቃድ ደም ለጋሾች ቀን በዓል ከሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መከበር ይጀምራል፡፡ በኢትዮጵያም እስከ ጳጉሜ 6 ቀን ድረስ በተያዩ ዝግጅቶች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እና የእግር ጉዞዎችን በማድረግ፣ ለመደበኛ ደም ለጋሾች ዕውቅናና የተለያዩ ሽልማቶች በመስጠት፣ ከተለያዩ ክልሎች ጋር በደም ልገሳ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች በመሥራት፣ የሃይማኖት አባቶች እና አርቲስቶችን ያካተተ የደም ልገሳ ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ፡፡ በዓሉም ከሰኔ 11 እስከ 12 ድረስ በደብረ ታቦር ከተማ እንደሚከበር ብሔራዊ ደም ባንክ ሰኔ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

‹‹ምንም እንኳን ብዙ ውጫዊ ልዩነቶች ቢኖሩንም በሁሉም የደም ሥራችን የሚዘዋወረው አንድ ዓይነት ደም ነው፡፡ በበጐ ፍቀደኝነት ደም መስጠት ሕይወት የመስጠት ተግባር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ማንም ሊሰጠው ወይም ሊቀበለው የሚችለው ታላቅ ስጦታ ነው›› ብለዋል የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ማርጋሬት ቻን፡፡

በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 108 ሚሊዮን የደም ልገሳዎች ይካሔዳሉ፡፡ ከዚህ ግማሽ በመቶ የሚሆነው የደም ልገሳ የሚደረገው ከፍተኛ ገቢ ባላቸውና ከዓለም ሕዝብ ከ20 በመቶ የሚያንስ ሕዝብ ባላቸው አገሮች ነው፡፡ አማካይ የደም ልገሳ ምጣኔ ሲታይም ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ልገሳ ምጣኔ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው በዘጠኝ እጥፍ ከፍ ያለ ነው፡፡

በብዙ አገሮች ያለው የደም ፍላጐት ከአቅርቦት የሚበልጥ በመሆኑ በቂ ደም ማቅረብ ትልቅ ተግዳሮት ነው፡፡ የደም ጥራትና ደኅንነትን የማረጋገጥ ነገር እንዳለ ሆኖ በቂ የደም አቅርቦትን ማረጋገጥ የሚቻለው በዘላቂ የበጐ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ መሆኑ ዘወትር ይገለጻል፡፡ መደበኛ በጐ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ደኅንነቱ የተጠበቀ ደም አቅርቦት መሠረት እንዲሆኑ ይህም የሚሆነው በደም ትራንስፊውዥን ወቅት ሊተላለፉ ከሚችሉ ኢንፌክሽኖች የራቁ ናቸው ተብሎ እንደሚታሰብ የዓለም ጤና ድርጅት በደም ለጋሾች ቀን ያወጣው መግለጫ ያስቀምጣል፡፡

በዓለም ላይ 25 አገሮች የተለገሰ ደምን እንደ ኤችአይቪና ሔፒታይተስ ቫይረሶች እንደማይመረምሩ ይህም በቴስት ኪት፣ በባለሙያ እጥረት፣ በቴስት ኪቶች የወረደ ጥራት ደረጃ ወይም በሌሎች የላብራቶሪ መሣሪያዎች እጥረት ሊሆን እንደሚችል በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አገሮች መደበኛ የበጐ ፍቃድ ደም ልገሳ ሥርዓት እንዲዘረጉ ያበረታታል፡፡ በአሁኑ ወቅት 62 የሚሆኑ አገሮች በበጐ ፍቃድ ደም ልገሳ ሙሉ በሙሉ የደም ፍላጐታቸውን ማሟላት ሲችሉ 34 ደግሞ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነውን የደም ፍላጐታቸውን ከዘመድ በሚገኝና በክፍያ በሚደረግ ልገሳ የሚሸፍኑ ናቸው፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...