Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ያገቡ የሐመር ሴቶችና ጌጣ ጌጣቸው

ትኩስ ፅሁፎች

 (ተድላ ገበየሁ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

*****

ጥሬ ጨው

መስለውኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸው
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨትመሰለቅመደለዝመወቀጥ
መታሸትመቀየጥ
ገና እሚቀራቸው
እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው

ደበበ ሰይፉ

*****

ኧረ የልጁ ነገር ከምን ደረሰ?

አንዲት እናት ልጅዋ በእኩለ ሌሊት ነቅቶ እያለቀሰ ስላስቸገራት ‹‹ዝም በል አንተ ለቅሶህንም አላቆም ካልህ አውጥቼ ለጅብ ነው የምሰጥህ፡፡ ና ብላው አያ ጅቦ›› ስትል ልጁ ፈርቶ ዝም አለ፡፡ ነገር ግን ለካስ አንድ ጅብ በጓሮ በኩል ደፍጦ ሲያዳምጥ ካሁን አሁን አውጥተው ይጥሉታል  ብሎ በመጠበቅ ላይ ነበርና በር ተንኳኳ፡፡ ‹‹ማነህ?›› ሲባል፣ ‹‹ኧረ የልጁ ጉዳይ ከምን ደረሰ?›› አለ ይባላል፡፡

  • መክብብ አጥናው ‹‹ሁለገብ የአዕምሮ ማዝናኛ›› (2005)

*****

ነፋስ አመጣሽ ዣንጣላ ሰው ገደለ

በአሜሪካ ቨርጂኒያ ባህር ዳርቻ ነፋስ ያመጣው ዣንጣላ የ55 ዓመት ሴትን መትቶ መገደሉን ፖሊስ እንደገለጸ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ሎቲ ሚሼል ቤልር የተባሉት ሴት ቨርጂኒያ ባህር ዳርቻ ላይ ነፋስ እያገላበጠ ባመጣው ዣንጥላ ተመትተው የሞቱት ረቡዕ ዕለት ነበር፡፡ የተመቱት ደረታቸው ላይ በመሆኑ ወዲያው የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ሆስፒታል እንደደረሱ ግን ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ከዋሽንግተን 175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ቨርጂኒያ ባህር  ዳርቻ የሄዱት ሴት ባልተጠበቀ ሁኔታ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

****

ፌስቡክ ፊሊፒንስን ይቅርታ ጠየቀ

የፊሊፒንስን የነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መግለጫ ያስተላልፍ ዘንድ ሆምፔጁ ላይ በለጠፈው የተሳተ ምሥል አገሪቱን ይቅርታ እንደጠየቀ ዘ ሚረር ዘግቧል፡፡ በየዓመቱ ጁን 12 በሚከበረው የፊሊፒንስ የነፃነት ቀን ፌስቡክ የተለጠፈው ፎትግራፍ አገሪቱ ጦርነት ላይ መሆኗን የሚያመለክት በመሆኑና የአገሪቱ ዜጎችም ምሥሉን በመመልከት የተሳሳተና ያልተፈለገ መልዕክት መተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ፌስቡክ የአገሪቱ ሰንደቅዓላማ ነው ብሎ የለጠፈው ሰንደቅ በትክክልም የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ አይደለም፡፡ ከዚህም ባለፈ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ‹‹አገሪቱ ጦርነት ላይ ነች›› የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ የቀለም አደራደር ያለው ነው፡፡ በዚህም ‹‹መልካም የነፃነት ቀን ለመላው የፊሊፒንስ ዜጎች ጤና፣ ደስታና ብልጽግና›› የሚለው የፌስቡክ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ተቃራኒ መልዕክት ባነገበ ምሥል ታጅቦ ወጥቷል፡፡

****

በሩ ግን አልተዘጋም

በአንድ መንደር ውስጥ አግብታ ብዙም ሳትቆይ ባሏን በሞት የተነጠቀች አንዲት ሴት ትኖር ነበር፡፡ አጠገቧ ዓይኗን የምታሳርፍባትና የምታጽናናት ብቸኛ ልጅ ነበረቻት፡፡ አንድ ልጇንም በርኅራኄና በፍቅር አሳደገቻት፡፡ ይሁን እንጂ በጥንቃቄ ብታሳድጋትም ልጇ ካደገች በኋላ የበለጠ ወደ ዓለም አዘነበለችና መንደሯን ለቅቃ ወደ ዋናው ከተማ ጥላት ኮበለለች፡፡ የልጅቷ እናት በሐዘን ተሰብራ ልጄ ከዛሬ ነገ ትመለስ ይሆናል ብላ ብትጠብቃትም እሷን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡

የኮበለለችው ልጇ እንድትመለስ ሌትና ቀን እየጸለየች ዓመታት አለፉ፡፡ አንድ ምሽት አንድ የእግር ዱካ ድምፅ ወደ ቤቷ በሚወስደው ጠባብ መተላለፊያ እየተቃረበ ሲመጣና ወደ በሩም ተጠግቶ የበሩን እጀታ እየፈራ እየተባ ሲነካ ሰማች፣ እጀታውም ድምፅ አሰማ፡፡ በእንቅልፍ ሰመመን እንዳለች አንድ ሰው ወደ ውስጥ መዝለቁን እናት ትሰማና ካልጋዋ ተፈናጥራ በመነሳት ወደ በሩ ታመራለች፡፡ የኮበለለችው ልጇ ናት፡፡ ልቧ በደስታ እየዘለለ ልጇን በፍቅር በእቅፏ ውስጥ ወሸቀቻት፡፡ እንደተቃቀፉም፣ ልጇ፣ ‹‹እማዬ፣ በዚህ በእኩለ ሌሊት ለምን በሩን አልቆለፍሺውም?›› ብትላት፣ እናት የልጇን ጸጉር እየደባበሰች፣

‹‹ልጄ ሆይ፣ አንቺ ከኮበለልሽበት ቀን ጀምሮ ምናልባት አንድ ቀን ስትመለሺ ልትቀበልሽ ሁሌ ዝግጁ የሆነች እናት እንዳለሽ እንድታውቂና ሳታመነቺ እንድትገቢ በማሰብ በሩ በቀንም ሆነ በሌሊት ተቆልፎ አያውቅም›› ስትል መለሰችላት፡፡

  • ኃይሌ ከበደ ‹‹ምስካይ›› (2004)

 

 

 

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች