Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመከላከያ ሚኒስቴር ከቱርክ ጋር ያደረገው ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ሊፀድቅ ነው

መከላከያ ሚኒስቴር ከቱርክ ጋር ያደረገው ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ሊፀድቅ ነው

ቀን:

የመከላከያ ሚኒስቴር ከቱርክ መከላከያ ሠራዊት ጋር በወታደራዊ ዘርፍ ለመተባበር የደረሱበትን ስምምነት ለማፅደቅ ፓርላማው ስምምነቱን ለውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መራ፡፡

ስምምነቱን በ1998 ዓ.ም. የፈረሙት በኢትዮጵያ በኩል ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የነሱ ሲሆኑ፣ በቱርክ በኩል ደግሞ የቱርክ አቻቸው ጄኔራል ሒልሚ ኡዝኩክ ናቸው፡፡

የትብብር መስኮቹ በወታደራዊ ሥልጠና፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ በአየር ኃይል፣ በምድር ጦርና ሎጂስቲክሰን መሠረት ያደረጉ ሆነው በሁለቱ አገሮች ስምምነት መሠረት ተጨማሪ ትብብሮች ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የሚኖረውን ፋይዳ አስመልክቶ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ አቶ አማኑኤል አብርሃም በሰጡት ማብራሪያ ቱርክ በምድር፣ በአየርና በባህር የተደራጀ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ካላቸው የዓለም አገሮች ውስጥ የምትመደብ እንደመሆኗ ከዚህ አንፃር የአገራችንን ወታደራዊ የሰው ኃይል ብቃትን የበለጠ ማሳደግ እንደሚያስችለው ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ የምትገኝበት ቀጣና ውስብስብና የተለያዩ የሽብር ቡድኖችና የአሸባሪዎች እንቅስቃሴና የተለያዩ የእርስ በርስ ግጭቶች የሚስተዋሉበት በመሆኑ፣ ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ካላት ከቱርክ ጋር የሚደረግ ወታደራዊ ትብብር የሽብር እንቅስቃሴንም ሆነ የፀጥታ ችግሮችን ለመግታት በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መረጃዎችንና ልምዶችን ለመለዋወጥ አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፤›› በማለት ከስምምነት ማፅደቂያው አዋጅ ጋር አባሪ የተደረገው ሰነድ ያስረዳል፡፡ የውጭ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር ከተመለከተው በኋላ በፓርላማው ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...