Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ከማለት ራስን ማየት

ቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ከማለት ራስን ማየት

ቀን:

ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ ሊሰጥ የነበረው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብሔራዊ ፈተና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሾልኮ በመውጣቱ የአገር አቀፉ ፈተና መቋረጡንና ወደ ሰኔ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. መዛወሩን በትምህርት ሚኒስትሩ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ይህ ከመደረጉ ከአንድ ቀን በፊት ግን እኚሁ የትምህርት ሚኒስትር ፈተናው መሰረቁ ሐሰት እንደሆነና የፈተናው ሒደት በሰላም እንደሚከናወን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡

በዚህ አኳኋን የፈተና መስተጓጎል በኢትዮጵያ የትምህርት ሒደት ታሪክ ሲከሰት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ ሁኔታው ተፈታኝ ተማሪዎችን፣ ወላጆችንና ዜናውን ያዳመጠውን ሕዝብ በሙሉ አሳዝኗል፡፡ በተከሰተው ችግር በሚሊዮን የሚቆጠር የአገር ሀብትና ጊዜ ባክኗል፡፡ በገንዘብ የማይተመን የተፈታኝ ተማሪዎችና ቤተሰቦች ሞራል ተነክቷል፡፡

በአሠራር ላይ ምን ያህል የመዝረክረክ ሁኔታ እንዳለ ከዚህ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ የፈተና መስተጓጎል መንግሥትን ኃፍረት ላይ የጣለና በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ያሳጣ በመሆኑ፣ በመልካም አስተዳደር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየጊዜው ሲገልጹ እንደሰማነው ‹‹ከዚህ በኋላ በሚታዩ ብልሹ አሠራሮች ላይ ተጠያቂነት እንደሚኖር›› እንጠብቃለን፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል ገብተዋል፤ ‹‹የሞት ሽረት ትግል›› እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ሕዝቡን ይቅርታ በመጠየቅ ብቻ የሚታለፍ ድርጊት ሳይሆን፣ ሕዝቡ ተገቢ የሆነና የማያዳግም አስተዳደራዊ ዕርምጃ በሚመለከታቸው ላይ ሁሉ ተወስዶ ማየትን ይፈልጋል፡፡ ዕርምጃውም ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ሳይሆን የዕርምጃው ክንድ ግንዱ ላይ ሲያርፍ የምናይበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በሠለጠነው ዓለም ግን እንደዚህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሥራቸውን በፈቃዳቸው ይለቃሉ፡፡ ሥራችንን በአግባቡ አልሠራንም ከሚል መነሻ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ቤትን ክፍት ትቶ ተዘረፍኩ ማለት የሚያዋጣ ሰበብ ሊሆን አይችልም፡፡

(ማቴዎስ ሸመሎ፣ ከሐዋሳ)

በቫት ማጭበርበር በሰፊው ቀጥሏል

ማንኛውም የቫት ተመዝጋቢ ነጋዴ ለሚሸጠው ዕቃ የቫት ደረሰኝ መሰጠት እንዳለበት በሕግ ተደንግጓል፡፡ ይህንን ኃላፊነታቸውን አውቀው በሕጋዊ መንገድ የሚሠሩ ነጋዴዎች ቢኖሩም፣ ከዚህ በተቃራኒ የሚሠሩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ይህም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሰፊው ይስተዋላል፡፡

 በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ቫት የቀረ እየመሰለ መጥቷል፡፡ ማጭበርበሩ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው ወገን ለሚሸጡት ዕቃ 15 በመቶ ቫት እየጨመሩ ደረሰኝ ግን የማይሰጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሕዝቡንና መንግሥትን ያጭበረብራሉ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 200 ብር ቢሆን 15 በመቶ ቫትን ጨምረው 260 ብር ይቀበላሉ፡፡ በዚህም ከእያንዳንዱ ገበያተኛ 60 ብር በሕገወጥ መንገድ ይሰበስባሉ ማለት ነው፡፡ ከአንድ በሬ ከሚያገኙት ትርፍ በተጨማሪ በቫት ስም ስንት ብር በተጭበረበረ መንገድ እንደሚያጋብሱ ይታያችሁ፡፡

ሁለተኛው ወገን ደግሞ ገቢያቸው እንዳይታወቅና የሚጠበቅላቸውን ታክስ እንዳይከፍሉ ሁለት ዓይነት ዋጋ ለአንድ ዕቃ የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ገዥውን ‹‹በቫት ከሆነ ይህን ያህል ትከፍላለህ ያለ ቫት ግን ይህን ያህል ነው፤›› ብለው ያለ ቫት እንዲገዛ ይገፋፋሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ነጋዴዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዕቃዎችን የሚሸጡ ስለሆነ በመንግሥት ላይ የሚያደርሱት ኪሳራ ቀላል አይሆንም፡፡ ለዚህ ዓይነት ሕገወጥ ንግድ መስፋፋት ዋናው ተጠያቂ ገቢ ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግድ ድርጅት ውስጥ ለጥቆማ የሚረዱ ስልክ ቁጥሮች ቢቀመጡና ተከታታይ ክትትል ቢደረግ፣ በተወሰነ ደረጃ እንዲህ ያለውን ድርጊት መቀነስ ይቻላል፡፡ ሕዝቡንም ማስተማር ተገቢ ነው፡፡

(ግርማ አያሌው፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...