Tuesday, January 31, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

‹‹አለባብሰው ቢያርሱ …››?!

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ዴሞክራሲና የሕዝብን ሰብዓዊ ማስጠበቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአብዛኛው ጊዜም ከቀድሞ ሥርዓት ጋር ራሱን በማነፃፀር የተሻለ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅና ዴሞክራሲ በአገሪቷ ላይ እንደሰፈነ ይደሰኩራል፡፡ ሆኖም ግን አሁን ዜጐች በሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተሰቃዩ እንደሆነ የማይታበይ ሐቅ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ስንል በአገሪቱ ከዚህ ቀደም ለዘመናት ሰፍኖ የነበረው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምንም አልተሻሻለም ማለታችን አይደለም፡፡

እንደሚታወቀው የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማሻሻል የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ ሰብዓዊ መብትን ለማሻሻል የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችንና የዴሞክራሲ ተቋማትን አቋቁሟል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ተቋማት ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ በሥራቸው ላይ ከሕዝብ የሰላ ትችት ይቀርብባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ተቋማቱ ገለልተኝነታቸውን ጠብቀው ከሕዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ እየተወጡ አለመሆኑን ነው፡፡

ለዚህም ማሳያ ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ማለትም እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎች  የሚያወጡት ሪፖርት በሕዝብ ዘንድ የበለጠ ተሰሚነት እያገኘ መምጣቱ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከባለቤቱ ያወቀ ምንድን ነው እንዲሉ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና ከኢትዮጵያዊ ተቋማት በተሻለ የሕዝቡን የሰብዓዊ መብት ችግርና የጉዳዩን አንገብጋቢነት ማንም ሊረዳው አይችልም፡፡

ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ የኦሮሚያና የአማራ ክልል አካባቢዎች በተነሱት ግጭቶች ሳቢያ የበርካታ የሰው ሕይወት ከማለፉም ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመት ተከስቷል፡፡ እነዚህን ግጭቶች ተከትሎ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰፊ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ እንደዚህ ዓይነት ሰፋ ያለና እስካሁን እምብዛም ያልተለመደ ሪፖርት ለማቅረብ በርካታ ወራትን መፍጀቱ በብዙዎች አስወቅሶታል፡፡ ምንም እንኳን ኮሚሽኑ ባቀረበው ሪፖርት በመንግሥት ላይ ጠንከር ያለ ትችት የሰነዘረ ቢሆንም፣ አሁንም ግን በግጭቱ ላይ የታዩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በማሳየቱ ረገድ ትችት ቀርቦበታል፡፡

ለምሳሌ ያህል የኦዲተር ጀነራል ቢሮ በየዓመቱ በሚያቀርበው ሪፖርት በመንግሥት አሠራር ላይ ከፍተኛ የሆነ ግድፈቶችን እየነቀሰ ያወጣል፡፡ ሆኖም ግን ከዓመት ዓመት እንደሚታየው ችግሮቹ እየተባባሱ ሲሄዱ እንጂ ሲሻሻሉ አይስተዋልም፡፡ በአንፃራዊነት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኦዲተር ጀነራል እንኳን ያክል ተከታታይ ሪፖርቶችን ሲያወጣ አይታይም፡፡ ይህም በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር ጥልቀት በግልጽ ያሳያል፡፡ ምክንያቱም በአገሪቱ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተካሄዱ እንዲህ ዓይነት ሪፖርት ለማውጣት ግጭቶችን ብቻ መጠበቁ፣ መሠረታዊ የሆነ ችግር እንዳለ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ከፖለቲካ ዲስኩር የዘለለ ሆኖ ለማየት ብዙዎች ይናፍቃሉ፡፡ ለዚህም ማሳያ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደሚሰማው ጥቂት የማይባሉ የፀጥታና የሕግ አስከባሪ አካላት በግዴለሽነትና በማንአለብኝነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጐች ላይ ይፈጽማሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት በየመንገዱ የሚታይና በሕዝብም ምስክርነት የሚሰጥበት ነው፡፡ አንዳንድ የፀጥታና የሕግ አስከባሪ አካላት ዜጐች ላይ አካላዊ ጉዳት ሲያደርሱም ይሰማል፡፡ እነዚህ አካላት ሕግን ለማስከበርና ሕዝብን ለመጠበቅ የሚሠሩ መሆናቸው እየታወቀ፣ በተቃራኒው የሚያስከብሩትን ሕግ ሲጥሱ ይታያል፡፡ በአንድ በኩል ይህ ለእነዚህ አካላት የሚሰጠው ሥልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ደካማ መሆናቸው ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ አካላት ሕግን እንዳይተላለፉ ተገቢው ቁጥጥር የማይደረግባቸውና ተላልፈውም ሲገኙ ተገቢው ዕርምጃ የማይዋሰድባቸው መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም መንግሥት የሰብዓዊ መብት ችግርን ለመቅረፍ ቁርጠኝነቱ ካለው መጀመር ያለበት ከዚህ ነው እንላለን፡፡

በሌላ ረገድ ሕዝቡ ራሱ መብቱንና ግዴታውን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት እንላለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁን ኃላፊነት የሚወስደው መንግሥት ራሱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ሕዝብን የማንቃት፣ የማስተማርና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሠራት አለበት፡፡ ይኼም ሲባል ይህ ሥራ በመንግሥት ብቻ የሚሠራ አይደለም፡፡ መልካም የሚሆነውማ አገር በቀል ሲቪል ማኅበራት፣ የሚዲያ ተቋማትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በስፋት ሲሳተፉበት ነው፡፡ እነዚህ አካላት የታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ድረስ በመዝለቅ ዜጐች በቂ የሰብዓዊ መብት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡

ሆኖም ግን መንግሥት በቀደሙት ጊዜያት ባወጣቸው ሕጐች በተለይ አገር በቀል የሲቪል ተቋማት መዳከማቸው የማይካድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሰብዓዊ መብት ማስከበሩ ሥራ፣ በመንግሥት ጫንቃ ላይ እንዲያርፍ አስገድዷል፡፡ ስለዚህ መንግሥት ይኼን ኃላፊነቱን በብቃት ካልተወጣና የሰብዓዊ መብት ጉዳይን በፖለቲካ መነፅር ማየት ካልተወ ችግሩን መቅረፍ የማይታሰብ ነው፡፡

ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት በኢኮኖሚያዊና በማኅበራዊ ዘርፉ ስኬትን አስመዝግቤያለሁ ሲል ይሰማል፡፡ እንደዚህም ስኬቶች በዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀር ተመስክረውለታል፡፡ ሆኖም ግን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር እነዚህን ስኬቶች ጥላሸት እንደመቀባት ነው፡፡ ይህም በአንድ እጅ እየሠሩ በሌላኛው እጅ ማፍረስ እንዳይሆን ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህም መንግሥት በአገሪቱ የተንሰራፋውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረፍ ሪፖርት ከማውጣት ባለፈ፣ ጠንከር ያለ ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ተረቱ አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንደሚል፣ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ችግር አንገብጋቢነት ተገንዝቦ፣ አፋጣኝ የሆነ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል፡፡        

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

ለልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ተፈቀደ

የገንዘብ ሚኒስቴር በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በሎጀስቲክስ፣ በኮንስትራክሽን፣ የባለኮከብ ሆቴሎች...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እንዲሠማሩ የሚፈቅድ መመርያ እየተዘጋጀ ነው

በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣...

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...

ለልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ተፈቀደ

የገንዘብ ሚኒስቴር በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በሎጀስቲክስ፣ በኮንስትራክሽን፣ የባለኮከብ ሆቴሎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የምግብ ችግር አገራዊ ሥጋት ስለደቀነ ፈጣን ዕርምጃ ይወሰድ!

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ልጆችን አቅም በብርቱ እየፈተኑ ያሉ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ከችግሮቹ ብዛት የተነሳ አንዱን ከሌላው ለማስቀደም የማይቻልበት ደረጃ ላይ የተደረሰ ቢሆንም፣ የምግብና የሰላም...

ፖለቲካና ሃይማኖትን እየቀላቀሉ በእሳት መጫወት አይቻልም!

ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ ከሚሹ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ሃይማኖት ነው፡፡ የሃይማኖት ጉዳይ ለተቋማቱና ለምዕመናኑ ብቻ የተተወ ነው፡፡ በሥራ ላይ ባለው ሕገ መንግሥትም መንግሥትና ሃይማኖት...

አገር የጥፋት ቤተ ሙከራ አትሁን!

መንግሥት አገር ሲያስተዳድር ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ የሚለዋወጡ ስትራቴጂዎች እንደሚኖሩት ዕውን ቢሆንም፣ በየጊዜው መዋቅሮችንና ፖሊሲዎችን መለዋወጥ ግን አይችልም፡፡ ‹‹ሁሉን መርምሩ የተሻለውን ያዙ›› የሚለው መጽሐፍ...