Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናትዴትና አረና በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

ትዴትና አረና በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

ቀን:

አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ (አረና) እና በቅርቡ ወደ አገር ቤት የተመለሰው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ (ትዴት) በጋራ ለመሥራትና በሒደት ደግሞ ወደ ውህደት ሊያደርሳቸው የሚያስችላቸውን ስምምነት፣ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. መፈራረማቸውን የአረና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋይ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

ስምምነቱን በአረና በኩል ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጎይቶም ፀጋይ፣ እንዲሁም በትዴት በኩልም እንዲሁ በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን መፈራረማቸው ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት ሁለቱ ፓርቲዎች በሚያግቧቧቸው የጋራ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የተስማሙ ሲሆን፣ በሒደትም በጋራ የመሥራቱ ነገር እስከ ውህደት እንደሚደረስ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተቀብሎ አገር ውስጥ የገባው ትዴት፣ አገር ውስጥ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ዝርዝር ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውና ሐሙስ የተፈረመው ስምምነትም የዚሁ ድርድር ውጤት መሆኑን አቶ ጎይቶም አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳን ውይይቶቹ ሲካሄዱ የነበሩት ትዴት አገር ቤት ከገባ በኋላ ቢሆንም፣ ሁለቱ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ብሎም ቢሆን ኢመደበኛ ግንኙነትና ውይይቶች እንደነበራቸው ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የተፈረመው በጋራ የመሥራት ስምምነት በዋነኛነት በአራት መሠረታዊ ነጥቦች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ እነዚህም የመሬት፣ የብሔርና የአንቀጽ 39፣ እንዲሁም በአጠቃላይ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ጉዳዮችና ተዋናዮችና የርዕዮተ ዓለም ጉዳዮችን የተመለከቱ እንደሆኑ አቶ ጎይቶም አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት የመሬት ጉዳይን በተመለከተ ሁለቱ ፓርቲዎች አንድ አቋም በመያዝ መሬት የሕዝብ ነው በሚለው ሐሳብ ተስማምተው፣ ይኼንንም ተፈጻሚ ለማድረግ በጋራ እንደሚሠሩ ተገልጿል፡፡

‹‹በአተገባበር ላይ የተለያዩ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የግለሰብ ሊኖር ይችላል፣ የመንግሥትም ሊኖር ይችላል፣ እንዲሁም የማኅበረሰብም ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን እንደ አጠቃላይ መርህ መሬት የሕዝብ ነው በሚለው ላይ ተስማምተናል፤›› በማለት አቶ ጎይቶም አስረድተዋል፡፡

የብሔርና የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 39 በተመለከተ ደግሞ የብሔር መብት በተሟላ መንገድ መከበር አለበት በሚለው ላይ ሁለቱም መስማማታቸውን፣ ነገር ግን ዋናው ነገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመገንባት የሚመለሱ ጥያቄዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹አንደኛ መንግሥት መገንጠል መፍቀድ አለመፍቀዱ አይደለም ዋናው ችግር፡፡ ዋናው ችግር ዴሞክራሲያዊ ከመሆንና ካለመሆን ጋር የተያያዘ እንጂ፡፡ ችግሩም በዚህ መንገድ መፈታት አለበት፡፡ ነገር ግን የመገንጠል የመፍትሔ አቅጣጫ ከማስቀመጥ መወጣት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ሥር ሆነን ችግሮችን መፍታት መልመድ አለብን፤›› ሲሉ አክለው አብራርተዋል፡፡

አጠቃላይ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ጉዳዮችና ተዋናዮችን በተመለከተ ደግሞ በአገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መተባበር በሚለው ጉዳይ፣ ሁለቱም ፓርቲዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል ‹‹ከሌሎች ጋር በመተባበር ችግሮቻችንን በኢትዮጵያ ሥር ሆነን ነው የምንፈታው ስንል፣ እኛ በትግራይ ክልል ብንደራጅም ሌሎችም ያስፈልጉናል በሚል አቋም ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ርዕዮተ ዓለምን በተመለከተ ደግሞ ምንም እንኳን ሁለቱ ፓርቲዎች የሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም የተለያየ ቢሆንም፣ ማለትም አረና ሊበራል ዴሞክራሲ ትዴት ደግሞ ሶሻል ዴሞክራሲ እነዚህ ልዩነቶች እንቅፋት እንደማይሆኑ አቶ ጎይቶም ገልጸዋል፡፡

‹‹የሁለቱን ፓርቲዎች የፖለቲካ ፕሮግራሞችና ዓላማ በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ በዚህም መሠረት ከስምምነት ደርሰናል፡፡ ከዚህ አቅጣጫ ስንመለከተው ርዕዮተ ዓለም የስም ጉዳይ ነው የሚሆነው፤›› ብለዋል፡፡

ሁለቱ ፓርቲዎች የጋራ መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀታቸውን የገለጹት አቶ ጎይቶም፣ ቀጣይ ሥራዎችን ለማከናወን የሚቀረው ትዴት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አማካይነት ሕጋዊ የመሆን ጉዳይ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

አረና ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባል ፓርቲዎች መሀል አንዱ ሲሆን፣ የተመሠረተው ከ1993 ዓ.ም. የሕወሓት ክፍፍል በኋላ ከፓርቲው በተባረሩ ነባር የሕወሓት ታጋዮች አማካይነት ነው፡፡ በተመሳሳይ  ትዴት ደግሞ በቀድሞው የሕወሓት ሊቀመንበር አረጋዊ በረኸ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ከ24 ዓመታት በፊት በውጭ አገር የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...