Sunday, December 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ በ6.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በገንዘብ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሚመራው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ፣ በ6.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገነቡ የሚታሰቡ 17 ሜጋ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችና የፍጥነት መንገዶች ቅድሚያውን ወስደዋል፡፡

  በቅርቡ ሥራ የጀመረው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ፣ በጋራ እንዲገነቡ ውሳኔ የሰጠባቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚጠይቁና ከ3,000 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 14 ሜጋ ፕሮጀክቶን ጨምሮ፣ ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጣባቸው ሦስት የፍጥነት መንገዶች በጠቅላላው በ6.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቁ ታውቋል፡፡

  በገንዘብ ሚኒስቴር ሥር የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ታፈሰ (ዶ/ር) ለሪፖርተር በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ መንግሥት ከግሉ ዘርፍ በተለይም ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እንዲገነቡ በቦርድ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ በውኃና በፀሐይ ኃይል የሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት የሚያስችሉ ናቸው፡፡  በተጨማሪም 357 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የፍጥነት መንገዶችም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ እንዲገነቡ መወሰኑን ተሾመ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

  በአጋርነት እንዲገነቡ ውሳኔ ከተሰጠባቸው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መካከል የገናሌ ዳዋ ቁጥር 5 እና 6፣ ጨሞጋ የዳ 1 እና 2፣ ሐለሌ ወራቤሳና ዳቡስ የተሰኙት የኃይድሮ ኃይል ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 የኃይድሮ ኃይል ማመንጫን ለመገንባት የእንግሊዝና የፈረንሣይ ኩባንያዎች የተጣመሩበትና 850 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተገለጸለት ፕሮጀክት እንደሆነ ይታወሳል፡፡

  የእንግሊዙ ግሎብሌክ ኩባንያ ከፈረንሣዩ ኮንቲንጀንት ቴክኖሎጂስ ጋር በመጣመር የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 ፕሮጀክትን ለመገንባትና በራሳቸው ለማስተዳደር ፍላጎት እንዳላቸው በማስታወቅ፣ የኩባንያዎቹ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸው ይታወሳል፡፡ የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 ፕሮጀክት ከውኃ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ፣ ከ20 እስከ 27 ሺሕ ሔክታር የሚገመት የእርሻ መሬት በመስኖ የማልማት ውጥን የተያዘለት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ የገናሌ ዳዋ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በገናሌ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ከታቀፉ ፕሮጀክቶች መካከል ይመደባሉ፡፡

  በፀሐይ ኃይል ረገድ እያንዳንዳቸው 100 ሜጋ ዋት ኃይል በመቀሌና በሑመራ የሚያመነጩ ሁለት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በአፋር፣ በድሬዳዋ፣ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልል የሚገነቡ ማመንጫዎች፣ ማሠራጫዎችና የኃይል ማስተላለፊያ ሰብስቴሽኖች ሥራ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ በአዋጅ የተቋቋመው የግልና የመንግሥት አጋርነት ቦርድ፣ በሰባት ሚኒስቴሮች ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተወከሉ ሁለት አባላት፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ኃላፊ ውክልና የሚመራ ነው፡፡

  እንደ ተሾመ (ዶ/ር) ማብራሪያ ከሆነ ፕሮጀክቱን በመከታተልና በማስፈጸም ረገድ የመንግሥት ተቋማት ወይም ፕሮጀክቱን ለመተግበር ከግል ኩባንያዎች ጋር የተደራደሩት መሥሪያ ቤቶች እንደሚመለከት ሲገለጽ፣ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ውል የሚገቡ የውጭ ኩባንያዎችም በአገሪቱ ሕግጋት እንደሚዳኙና ይህንንም በመቀበል እንደሚገቡ ተብራርቷል፡፡

  በገንዘብ ሚኒስቴር በሰብሳቢነት፣ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርን ጨምሮ ሰባት ሚኒስቴሮች፣ ከኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተወከሉ ሁለት የግሉ ዘርፍ ተወካዮች የሚሳተፉበት፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በጸሐፊነት የተካተተበት ቦርድ፣ በአማራጭነት የሚቀርቡ ፕሮጀክቶን ጠቀሜታ በመመዘን የሥጋት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑና በመንግሥት አቅም ብቻ ሊገነቡ የማይችሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ጋር በመደራደር እንዲገነቡ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሚና ከተጠሱት ኃላፊነቶች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች