Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለፓርላማው ሕንፃ ዕድሳት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታወቀ

ለፓርላማው ሕንፃ ዕድሳት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታወቀ

ቀን:

በቅርቡ አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን ለጀመረው አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ስብሰባ ለማድረስ የመሰብሰቢያ አዳራሹን ጨምሮ ለተለያዩ የሕንፃ ክፍሎች ዕድሳት ጥገና፣ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታወቀ፡፡ የፓርላማ የጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ምሥራቅ መኰንን (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከተገነባ በርካታ ዓመታት ያስቆጠረው ሕንፃ አጠቃላይ ጥገናና ዕድሳት የሚያስፈልገው ቢሆንም፣ ዋናውን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጨምሮ ለተወሰኑ የሥራ ክፍሎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ዕድሳት እየተደረገ ነው፡፡

በተለይ ዋናው የጉባዔው አዳራሽ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ለተካሄደው የፓርላማው የሥራ ዘመን መክፈቻ እንዲደርስ ጥገናውን የሚያከናውነው የሥራ ተቋራጭና በጽሕፈት ቤቱ ጭምር 24 ሰዓት በመሥራት፣ አዳራሹን በ45 ቀናት ውስጥ ታድሶ ለሁለቱ ምክር ቤተች የጋራ መክፈቻ ቀን ማድረስ መቻሉን ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

የዕድሳት ሥራው በሁለት ተከፍሎ ሲከናወን፣ በመጀመርያ ዙር የጉባዔ አዳራሹና የኃላፊዎች የሥራ ክፍሎች ዕድሳት በአብዛኛው ተጠናቋል፡፡ በሁለተኛው ዙር የሚደረጉት ቀሪ የዕድሳት ሥራዎች በአሁኑ ጊዜ በመካሄድ ላይ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የዕድሳት ሥራውን የሚያከናውነው አሸናፊ የሕንፃ ሥራዎች የተባለ የሥራ ተቋራጭ መሆኑን የገለጹት ምሥራቅ (ዶ/ር) ሥራው ያለ ጨረታ ስለመሰጠቱ ሪፖርተር ላነለሳቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ዕድሳቱን በአስቸኳይ ለማከናወን የጊዜ ጥበት ስለነበረና ተቋራጩም ሥራውን በሚፈለገው ቴክኖሎጂ ማከናወን እንደሚችል ስለታመነበት በልዩ ውሳኔ ያለ ጨረታ መሰጠቱን አረጋግጠዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የፓርላማው ሕንፃ ዕድሜ ጠገብና ታሪካዊ በመሆኑ እንዴት መጠገንና በምን ዓይነት ቴክኖሎጂ ታሪካዊነቱንና ደኅንነቱን ጠብቆ ማደስ እንደሚቻል፣ በአመራሩ ተመክሮበት ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ዕድሳቱን አቅዶ ወደ ሥራ ለመግባትም ሆነ ተቋራጭ ፈልጎ ሥራውን ለማስጀመር የነበረው ጊዜ ሁለት ወራት ብቻ በመሆኑ፣ በቀጥታ ሥራውን የሚያከናውን ድርጅት መፈለግ እንደሚገባ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም አሁን ዕድሳቱን እያከናወነ ለሚገኘው ተቋራጭ ሥራው መሰጠቱን ኃፊላዋ ተናግረዋል፡፡

ተቋራጩን ለመምረጥም መነሻ የሆናቸው ሌላኛው ምክንያት፣ ቀደም ሲል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (የአሁኑ ሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር) ያስዋቡ ወጣቶች መኖራቸው በተገኘነው መረጃ ነው ብለዋል፡፡ “የእዚህን ታሪካዊ ሕንፃ ደኅንነቱንና ታሪካዊነቱን በጠበቀ መንገድ በተፈለገው ፍጥነትና የቴክኖሎጂ አቅም በመታገዝ፣ እንዴት ማስዋብና ለሥራ ምቹ ማድረግ የሚችሉ ወጣቶችን የያዘ የሥራ ተቋራጭ መኖሩን ጽሕፈት ቤቱ በተሰጠው ምክረ ሐሳብ መሠረት ለወጣቶቹ ሰጥተናል፤” በማለት ያለጨረታ የተሰጠበትን ምክንያት አብራርተዋል፡፡

ሕንፃውም ዕድሜ ጠገብ ከመሆኑና ካለው ታሪካዊ ይዘት አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ ስለነበረበት ወደ ማደሱ ሥራ ከመገባቱ በፊት፣ ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር ውይይት መደረጉንና የባለሥልጣንም ይሁንታ በመቀበል ዕድሳቱ መጀመሩንም  አስረድተዋል፡፡

ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ክትትል በተጨማሪ የዕድሳት ሥራውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅርስ ጥበቃና የአንትሮፖሎጂ የትምህርት ክፍሎች የተመደቡ ባለሙያዎችም ክትትል እየተደረገለት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በጀቱን በተመለከተ ከሪፖርተር ለተነሳላቸው ጥያቄም በሰጡት ማብራሪያ፣ ‹‹ለዕድሳቱ ብለን ተጨማሪ በጀት ከመንግሥት አካል አልጠየቅንም፡፡ ምክር ቤቱ ካለው በጀት አብቃቅተን ነው የተጠቀምነው፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...