Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊደረጃ ሦስትና አራት የጡት ካንሰር ህሕክምናን በኢትዮጵያ መስጠት ፈተና ሆኗል

ደረጃ ሦስትና አራት የጡት ካንሰር ህሕክምናን በኢትዮጵያ መስጠት ፈተና ሆኗል

ቀን:

ደረጃ ሦስትና አራት የጡት ካንሰር ሕክምናን በአገር ውስጥ ለመስጠት ያለው የአቅም ውስንነት ፈተና መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የካንሰር ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስትና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ተናገሩ፡፡  

አራት ዓይነት የሕመም ደረጃዎች ያሉት የጡት ካንሰር በእናቶች ላይ የተጋረጠ ከባድ የጤና ችግር ሲሆን፣ ደረጃ ሦስትና አራት የጡት ካንሰር ደግሞ ታማሚዎች ከባዱን ሕመም የሚያስተናግዱበት ነው፡፡

ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳሉት፣ በካንሰር በሽታ ላይ ትኩረት ያደረገ ግንዛቤ የማስጨበጥና ሰዎች በሽታው እንደጀመራቸው ወይም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዳለ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ በሽታው ሥር ሳይሰድ እንዲታከሙ ማድረግን ያካተተ ስትራቴጂ እየተተገበረ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የጡት ካንሰር በአብዛኛው የሚታየው በ40 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ቢሆንም በ30 ዓመት ወይም ከዚህ ዕድሜ በታች ባሉ ሴቶች ላይም ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባር የካንሰር ኬር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ፕሮግራሙም በብዛት ተግባራዊ የሚሆነው ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው በሚገኙ ከተሞችና ገጠር አካባቢዎች ነው፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ 12 የመንግሥት ሆስፒታሎች የጡት ካንሰር ሕክምና እንደሚሰጥ፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ መሆኑን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የካንሰር ኦፊሰሯ ሲስተር ታከለች ሞገስ ገልጸዋል፡፡ ኅብረተሰቡ የጡት ካንሰር መንስዔዎችን እንዲያውቅና ራሱን እንዲከላከል ሲስተር ታከለች ጠይቀዋል፡፡ እናቶችም በወር አንድ ጊዜ የጡቶቻቸውን ዙሪያ በእጆቻቸው እየዳበሱ ማንኛውንም እብጠት ካገኙ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱም አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ሙሉጌታ፣ የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ የሴሎች መራባት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ከሰውነት ቁጥጥር ውጪ የሆነች አንዲት ሴል በተለያዩ ምክንያቶች ወደ እብጠት ትቀየራለች፡፡ እየተራባች እየሰፋችና አቅም እያገኘች ስትሄድም በጡት ውስጥ ትሠራጫለች፡፡

ከጡትም አልፋ ወደ ጡት ሽፋን ቆዳ ዘንድ ልትሄድ ትችላለች፡፡ በደረት ክፍል ወደ ውስጥ፣ ከዚያም ወደ ብብትና አልፎም ወደ የትኛውም የሰውነት ክፍል በተለይ ሳምባ፣ ጉበትና የጀርባ አጥንት ላይ ልትደርስ ትችላለች፡፡

እብጠቱ ሲሠራጭ ቆዳ ሊሸበሸብ፣ የጡት ጫፍ ደግሞ ወደ ውስጥ ሊሰረጉድ፣ ብብት አካባቢ እብጠት ሊያሳይ ይችላል፡፡ እየቆየ ሲሄድም የመቁሰልና የሕመም ስሜት ሊመጣ እንደሚችል ዶ/ር ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡ ሕመሙ ወደ ጀርባ ከተሠራጨ ደግሞ አጥንት ላይ የሕመም ስሜት ሊኖር፣ ወደ ሳምባ ከተዳረሰም ሳልና የመተንፈስ ችግር፣ አልፎ አልፎም ዓይን ቢጫ ሊሆን እንደሚችል ከዶ/ር ሙሉጌታ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ለሦስት ቀናት በቆየው የምርመራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ ለምርመራ ከመጡ እናቶች መካከል ጡቶቻቸው ላይ እባጭ የታየባቸው፣ ቤተሰቦቻቸው የጡት ካንሰር ያለባቸውና አጋጣሚው ሥጋት የፈጠረባቸው እንዲሁም ልዩ ልዩ ክትትል የሚያደርጉ ይገኙባቸዋል፡፡ ምንም ምልክት ያልታየባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና በዓመት አንዴ ወደ ጤና ተቋም እየሄዱ ክትትል እንዲያደርጉ ምክር እየተሰጣቸው ወደመጡበት እንዲሄዱ ሲደረግ፣ ምልክቱ የታየባቸው ደግሞ ለቀጣይ ምርመራ ፕሮግራም እንደተያዘላቸው ገልጸዋል፡፡  

ከጥቅምት 16 ቀን እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጥና የምርመራ ሥራ 800 ለሚጠጉ እናቶች የጡት ካንሰር ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...