Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ልናገርአክራሪ ብሔርተኝነት እንጂ ብሔርተኝነት ክፋት የለውም!

አክራሪ ብሔርተኝነት እንጂ ብሔርተኝነት ክፋት የለውም!

ቀን:

በሀብታሙ ግርማ

በዘልማድ አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን እየጠቀስን እገሌ እኮ ብሔርተኝነት ያጠቃዋል፣ ለአገር ሥጋት ነው፣ ወዘተ. እያልን መፈረጅ በተደጋጋሚ ከምታዘባቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ምልልሶች አንዱ ነው። ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን በብሔርተኝነት ስንፈርጅ ዕውን ብሔርተኛ የሚለውን ቃል መዝገበ ቃላታዊ ወይም ጽንሰ ሐሳባዊ ትርጉም ተረድተነዋል? ግለሰቦቹን የምንኮንንበት አግባብ ምንድነው? በምክንያት ወይስ የብየናችን መሠረት ግለሰባዊ ጥላቻ (Personal Animosity)፣ የዕውቀት ማነስ (Illiteracy)፣ የስሚ ስሚ (Heresay)፣ ወይስ. . . ?

ብሔርተኝነት ምን ክፋት አለው?!

- Advertisement -

በመሠረቱ ማኅበረሰባዊ የሆነ ጽንሰ ሐሳብን መረዳት ያለብን ከወል ወይም ከቡድን አንፃር እንጂ ከግለሰባዊነት አይደለም። እናም የአንድ ማኅበረሰብ ሥሪቶች (Social Fabrics) መገለጫዎች የጋራ ወይም ቡድናዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ተፈጥሯዊ የጋራ (ቡድናዊ) መገለጫ ከሆኑ የማኅበረሰብ ሥሪቶች መካከል ፆታ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ሃይማኖትና ብሔር ጥቂቶቹ ናቸው። እያንዳንዱ የማኅበረሰብ አባል ማንነት የእነዚህ ሁሉ ድምር ነው። ስለሆነም ብሔርተኝነት ማስቀረት የማንችለው፣ በትርጉምም ሆነ በጽንሰ ሐሳብ ሚዛን ክፋት የሌለው ከማኅበረሰባዊ ውቅሮች ወይም መገለጫዎች አንዱ ነው።

ነገር ግን በአማርኛ የፖለቲካ መዝገበ ቃላት ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከበዘበዝናቸው ቃላት መሀል ብሔርተኝነት የሚለውን ቃል አንዱ ነው። ብሔርተኛ የሚለው ቃል እንግልት ሁለት ገጽታ አለው:: አንደኛው የትርጉም ሲሆን፣ ሌላው የይዘት ነው። ከትርጉም አንፃር ብሔርተኝነት አሉታዊ ትርጉም የመስጠት፣ ከይዘት አንፃር ደግሞ የቃሉን መገለጫ የምንረዳበት አጥብበን ወይም አድሏዊ በሆነ መንገድ ነው። በአጠቃላይ ብሔር አንዱ የማኅበረሰብ (ሕዝብ) ክፍፍል መገለጫ ሲሆን፣ ብሔርተኝነት ማኅበረሰብ እስካለ ድረስ የማይቀር ማኅበረሰባዊ እውነታ ነው።

በብሔር መሰባሰብ ኢ ምክንያታዊ አይደለም!

የማኅበረሰብ ክፍሎች የጋራ በሚያደርጋቸው ነገር ማለትም በዘር፣ በብሔራቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በፆታቸው፣ ወይም በሙያቸው ከተጠቁ ልዩነቶቻቸውን ትተው የተጠቁበትን ነገር ይዘው ከጥቃት ራሳቸውን ለመመከት ምላሽ ይሰጣሉ። ምላሻቸው በተለያዩ መደበኛ ወይም ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች ሊሆን ይችላል። ታሪክ ከሚያነሳቸው ታላላቅ እውነቶች አንዱ፣ በቡድናዊ ጭቆናዎች ገፊ ምክንያት ጨቋኞችን ለመታገል የተደረጉ የፀረ ጭቆና ትግሎች ትልቁን ሥፍራ ይይዛል። ለአብነትም በዘር መሠረታቸው የተጨቆኑ የተሰባሰቡበት በአሜሪካ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግል፣ በኢኮኖሚ ደረጃቸው የተበዘበዙና ብዝበዛውን ለመታገል የተሰባሰቡበት የወዛደሮች ትግል ወይም የሶሻሊስት ንቅናቄ፣ ሃይማኖታቸውን መሠረት አድርጎ የተቃጣባቸውን ጥቃት ለመመከት የተቋቋሙ የሃይማኖት ንቅናቄዎች፣ በፆታ ክፍፍል በወንዶች ተጨቁነናል ያሉ ሴቶች የፆታ ጭቆናን ለመታገል በሚል የመሠረቱት የእንስታይ ንቅናቄ (Feminist Movement)፣ በብሔር ማንነታቸው የተበደሉ በብሔር ፖለቲካ አደረጃጀት መሰባሰብ፣ ወዘተ. መጥቀስ ይቻላል።

ተፈጥሮ ማለት እውነት ማለት ነው። እናም ብሔር ማኅበረሰባዊ እውነት ነው። ከብሔር ማዕቀፍ የሚወጣ ማኅበረሰብ የለም። ነገር ግን ሁሉም ሰው ብሔርተኛ ነው ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ በብሔር ማንነት የመጨቆንና ያለመጨቆን ጉዳይ ነው ብሔርተኝነትን የሚወስነው።

የብሔር ጭቆናን መታገል አክራሪ ብሔርተኝነትን መታገል ማለት ነው!

የትኛውም የፀረ ጭቆና ትግል አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ጭቆና ሰዎችን ወደ አክራሪነት ይመራል። የአክራሪነት መገለጫዎች የሆኑት ጥላቻ፣ ኢ ምክንያታዊነት፣ ፍርኃት፣ ጭካኔና የጭቆና ልጆች ናቸው። የጭቆና የበኩር ልጅ ጥላቻ ነው፡፡ ቀጥሎ ኢ ምክንያታዊነት ይወለዳል፡፡ ስሜታዊነትና ፍርኃት ደግሞ ይከተላሉ። የጭቆና የመጨረሻ ልጁ ጭካኔ ይባላል።  ከሁሉም የጥላቻ ልጆች ጭካኔ የተባለው ልጅ እጅግ አደገኛ ነው። ጭካኔ የሰብዓዊነት ወይም የማኅበረሰብ መሠረቶች የሆኑትን እምነት፣ ሞራልና ግብረ ገብን በመሸርሸር እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ማኅበረሰብ የመቆም ህልውን ይነፍጋል።

የአክራሪነት መሠረቱ ጭቆና በመሆኑ የትኛውም ዓይነት አክራሪነት ማለትም የፆታ፣ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የኢኮኖሚ፣ ወዘተ. ፍትሕንና እኩልነትን በማስፈን ጭቆናን በመታገል ይፈታል። ስለዚህ አክራሪ ብሔርተኝነትን ለመዋጋት ብሔርና ማንነትን መሠረት ያደረገ አድልኦ እንዳይኖር ወይም ጭቆናን በመታገል ይፈታል። በብሔር መደራጀት ብሔራዊ ጭቆናን ለመዋጋት አንዱ መንገድ ቢሆንም፣ በራሱ ግን ግብ አይደለም፡፡ ዓላማውም ብሔራዊ ጨቋኞችን መበቀል፣ ማሳደድ፣ ወይም መጨቆን አይደለም፡፡ ብሔራዊ ማንነትን ከማስከበርም አልፎ ለሌሎች ብሔራዊ ጭቆና ሥር ላሉ (ለሚገጥማቸው) ማታገያ ሐሳብ ማዋጣት ነው።

በመሆኑም በብሔር መደራጀቱ ግብ የሚሆነው ትግሉ በሐሳብ የተመራ ሲሆን ነው፡፡ ሐሳቡ አድጎና ዳብሮ ቢያንስ በየትኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ የብሔር ጭቆናን ለመዋጋት የሚችል ኃልዮት ለመገንባት የራሱ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉ ነው። ልክ የኢኮኖሚ ጭቆና የደረሰባቸውን የአውሮፓ ወዛደሮችን ለማታገል እነ ካርል ማርክስ ሳይንሳዊ ኅብረተሰባዊነት (Scientific Socialism) ኃልዮትን ነድፈው በዓለም ያሉ ጭቁን ወዛደሮችን ለማታገል እንደ ርዕዮተ ዓለም መሣሪያ እንደዋለው ማለት ነው። በአጠቃላይ በብሔር የመደራጀት ዓላማ የብሔረሰቡን ማንነታዊ ጭቆናን መታገል ቢሆንም፣ ግቡ ግን ከብሔሩ የተሻገረ መሆን አለበት ነው ነገሩ።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻው [email protected] ማግኘት ይቻላል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...