Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየላቀ የአሠራር ተሞክሮ ያላቸው ድርጅቶች ተሸለሙ

የላቀ የአሠራር ተሞክሮ ያላቸው ድርጅቶች ተሸለሙ

ቀን:

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ላይ ከተወዳደሩ 50 ተቋማት መካከል ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ 11 ተቋማት የዋንጫና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡ ተቋማዊ አመራርን፣ የደንበኞችን መስተንግዶ፣ ድርጅታዊ ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ አስተዳዳር፣ ውጤታማነትና የመሳሰሉትን መስፈርቶች መሠረት አድርጎ በተካሄደው ወድድሩ ላይ አሽናፊ የነበሩት በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ ለትርፍ የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ለአትርፍ ያልተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሲሆኑ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፣ የአማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ቆዳ አክስዮን ማኅበር፣ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪ፣ አርባምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ፣ ኤሌክትሮ ኮሜርሻል፣ ዳሽን ቢራ፣ ማይጨው ፓርቲክልስ ቦርድ ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር፣ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካና ሐርመኒ ሆቴል ናቸው፡፡

‹‹የአገራችን የኤኮኖሚ ዕድገት ልማት ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግሥት ብቻ የሚደረገው ጥራት በቂ ባለመሆኑ ለዕቅዱ ስኬታማነት ሁሉም የልማት አጋሮች የሚያደርጉት አስተዋፅኦና የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፤›› ያሉት ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ናቸው፡፡ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባትና የአገሪቱን ራዕይ ዕውን ለማድረግ ጥራትን መሠረት አድርጎ መሥራት ወሳኝ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ለምርትና አገልግሎት ጥራት የሚተጉ ድርጅቶች የሚበረታቱበት አዳዲስ ተቋማት የሚፈጠሩባቸውም በመሆናቸው ሊለመዱ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀው በዚሁ የሽልማት ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን መሐመድ ‹‹ተቋማቱ የተወዳደሩት እርስ በእርስ አይደለም፡፡ የተወዳደሩት ካዘጋጀነው የሥራ መመዘኛ አኳያ እንጂ፡፡ ለዚህም ነው 11 ተቋማት ከአንድ እስከ ሦስት ሊወጡ የቻሉት፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛ መስፈርቶችን ከግምት በማስገባት አገራዊ የጥራት መመዘኛ መስፈርቶች አዘጋጅቶ በወድድሩ ብልጫ ላገኙ ተቋማት የጥራት ሽልማት እንደሚሰጥ የሚናገሩት የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጀት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ ናቸው፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ፣ አሠራሩ የአገሪቱን ኩባንያዎች በዓለም አቀፍ አሠራር መሠረት ራሳቸውን እንዲፈትሹ ያደርጋል፡፡ ምርቶቻቸውና አገልግሎታቸውንም በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን ይረዳል፡፡ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ዕድገትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

ከስምንት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች በምርቶቻቸውና በአገልግሎትቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማገዝ ቀዳሚ ዓላማው ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ለተቋማት ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን፣ የምክር አገልግሎቶችን እንዲሁም አገር አቀፍ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት የተለያዩ አቅም የመገንባት ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለማወዳደር የሚያስችለው የራሱ መመዘኛ ማኑዋል በማዘጋጀት ተቋማትን ሲያወዳድር ቆይቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ባዘጋጃቸው ሦስት ውድድሮች ላይ 24 ተቋማት የድርጅቱን የተለያዩ ደረጃ ያላቸው የጥራት ሽልማቶች ማግኘት ችለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በግጭት ለተጎዱ ልጆች 80 ሺሕ መጻሕፍት ማሠራጨት መጀመሩን ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከትምህርት ቤት ለተስተጓጐሉ፣ በሥነ ልቦናና በሌሎች...

የም እና መስህቦቿ

በቱባ ሀገሬ የም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ239...

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...