Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየደቡብ ክልል ምክር ቤት የሦስት ዞኖች አዳዲስ የአስተዳደር እርከኖች አፀደቀ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሦስት ዞኖች አዳዲስ የአስተዳደር እርከኖች አፀደቀ

ቀን:

የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የሦስት ዞኖችና የ44 ወረዳዎች አዳዲስ የአስተዳደር እርከኖች አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባዔ ሃላባ ልዩ  ወረዳና ኮንሶ ልዩ ወረዳ በዞን፣ ጋሞ ጎፋ ዞን ደግሞ ለሁለት ተከፍሎ ጋሞ ዞንና ጎፋ ዞን ሆነው እንዲደራጅ የቀረበውን አዋጅ በ17 ተቃውሞ፣ በሦስት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ከሦስቱ ዞኖች በተጨማሪ 44 ተጨማሪ ወረዳዎች እንዲፈጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ እነዚህ አዳዲስ የአስተዳደሩ እርከኖች እንዲፈጠሩ ምክር ቤቱ የወሰነው የሕዝብ ብዛት፣ የወረዳ/ቀበሌ ብዛት፣ የመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የቆዳ ስፋትና የገቢ አቅም መሥፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ልዩ ወረዳ የነበረው ሀላባ ዞን ሆኖ ሲመሠረት ዌራ ዙሪያ፣ ድጀ ዌራና ድጀ የተባሉ ወረዳዎች፣ እንዲሁ ቁሊቶ ከተማን አካቶ ይደራጃል፡፡

ቀደም ሲል በሰገን ሕዝቦች ዞን ውስጥ ልዩ ወረዳ የነበረው ኮንሶ ዞን ሆኖ ይደራጃል፡፡ ኮንሶ ዞን በሥሩ ካራት ከተማ አስተዳደርን፣ ካራት ዙሪያ፣ ሰገን ዙሪያና ከና የተሰኙ የወረዳ መዋቅሮች ይኖሩታል፡፡

ጎፋ ዞን በሥሩ ስምንት ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን ደምባ ጎፋ፣ ገዜ ጎፋ፣ ዛላ፣ ኡባ ደብረ ፀሐይ፣ አይዳ፣ ሳውላ፣ መለኮዛና ጋዳ ወረዳዎች፣ እንዲሁም ሳውላና በልቂ የከተማ አስተዳደሮች ይኖሩታል፡፡

ጋሞ ዞን ደግሞ 13 ወረዳዎች የሚኖሩት ሲሆን አርባ ምንጭ ዙሪያ፣ ደረማሎ፣ ቁጫ፣ ዲታ፣ ካምባ፣ ምዕራብ ዓባያ፣ ጨንቻ፣ ቦንኬ፣ ሰሜን ቦንኬ፣ ጋርዳ ማርታ፣ ቦረዳና ምዕራብ ቁጫ ወረዳ፣ እንደሁም አርባ ምንጭ ከተማን ያስተዳድራል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ አዳዲስ የዞንና የወረዳ አደረጃጀቶችን በተመለከተ በየአካባቢው ከሕዝብ ጋር የሚደረገው ውይይት ሲጠናቀቅ፣ በክልሉ ምክር ቤት በሚሰጥ ውክልና መሠረት ወደፊት በመስተዳድር ምክር ቤቶች እንደሚወሰን ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...