Wednesday, May 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 938 ሚሊዮን ብር አተረፈ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከተመሠረተ አሥረኛ ዓመቱን የያዘው ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በታሪኩ ከፍተኛ የትርፍ ዕድገት በማስመዝገብ በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 938 ሚሊዮን ብር አተረፈ፡፡

ባንኩ ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ይፋ እንዳደረገው፣ የባንኩ የ2010 የሒሳብ ዓመት የትርፍ መጠን ከቀድሞው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ140 በመቶ በላይ ዕድገት አሳይቷል፡፡

በቀደመው ዓመት ባንኩ ከታክስ በፊት 391 ሚሊዮን ብር ያስመዘገበ ሲሆን፣ የባንኩ ትርፍ በአንድ ዓመት ልዩነት የ547 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለውን ትርፍ ማስመዝገቡ የባንኩን የ2010 የሒሳብ ዓመት የትርፍ መጠን የተለየ አድርጎታል፡፡

ባንኩ በሒሳብ ዓመት ያስመዘገበው የተጣራ ትርፍ 728 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ባንኩ ይፋ ባደረገው ሪፖርት የተመለከተ ሲሆን፣ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ145 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ያስመዘገበው የትርፍ ዕድገት ምጣኔ በባንክ ኢንዱስትሪው ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዚህም ምክንያት የባንኩ የትርፍ ክፍፍል ወደ 54 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

የ2010 በሒሳ ዓመት በአብዛኛው ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ሲሆን፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 19.9 ቢሊዮን ብር እንደደረሰና ጠቅላላ ሀብቱም 23.8 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተመልክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች