Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ኢትዮጵያ የምትባል አገር ያለችው መከላከያ ውስጥ ነው››

‹‹ኢትዮጵያ የምትባል አገር ያለችው መከላከያ ውስጥ ነው››

ቀን:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው ጎንደር ሲደርሱ፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ውይይታቸው ወቅት ከቀረበላቸው ጥያቄ አንዱ በመከላከያ ውስጥ የአንድ ብሔር የበላይነት ስላለ እንዴት ይታረቅ የሚል ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በግልጽ ይነገር ከተባለ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ያለችው መከላከያ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ በሰጡት ምላሽ አልተነገረም እንጂ አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበው መከላከያን ሪፎርም ማድረግ ላይ ያተኮረው እንደነበር፣ በአንድ ዕዝ ውስጥ ከአንድ ብሔር ሁለት ሰው እንዳይኖር መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

‹‹ካሉን ዕዞች በየትኛውም ዕዝ ከአንድ ብሔር ሁለት ሰው የለበትም፡፡ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጣ ዕዝ ነው ያቋቋምነው፡፡ ምክንያቱም መከላከያ ይተች የነበረው ከታች ሳይሆን ከላይ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህም ለመጀመርያ ጊዜ በመከላከያ ውስጥ ሁሉም ብሔር ኮሚቴ ሆኖ የሚሠራበት አሠራር መተግበሩን ገልጸዋል፡፡ የዚህ ውጤት ቆይቶ የሚታይ እንደሆነም አክለዋል፡፡

የመከላከያ አቅሙ ጠላት ጥቃት እንዳይፈጽም የሚያስቀር ስለሆነ ብቃትን የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህም ድብቅ የሆነ አደረጃጀት እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በዚህ ንግግራቸው፣ ‹‹በግልጽ ንገረኝ ካላችሁ የመጨረሻ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ያለችው መከላከያ ውስጥ ነው፤›› ብለው፣ ‹‹ሌላውማ ስለቀበሌውና ስለቤተሰቡ የሚያላዝን ነው ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ፤›› ብለዋል፡፡  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጎንደር ከማቅናታቸው ከሰዓታት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የመከላከያ ሠራዊትን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በከፍተኛ ግለት እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረዳታቸውን አስታውቋል፣ ‹‹በዋነኛነት በመከላከያ አመራር ልህቀት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ በተለይ የመከላከያ ልህቀትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአመራር ክህሎቶች፣ የግዳጅ አፈጻጸም ሒደት ላይ ኃይልና ሥልጣንን በተገቢው መጠን፣ አግባብና ሁኔታ በመጠቀም ቅቡልነት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ ላይ ውይይት አድርገዋል፤›› ብሏል፡፡

መግለጫው አክሎም የመከላከያ ሠራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ የባህር ኃይል አደረጃጀትን አካቶ፣ እንዲሁም ወደፊት የሳይበርና የሕዋ (Space) ምኅዳሮችን ለማካተት በሚያስችል መንገድ መሻሻሉን ገልጿል፡፡

‹‹ዘመናዊ ዓውደ ውጊያ በሚጠይቃቸው አምስቱ ምኅዳሮች (ምድር፣ አየር፣ ባህር፣ ሳይበርና ሕዋ) ዝግጁ የሆነ መከላከያ ሠራዊት የመገንባት ሒደት ተጀምሯል፤›› ሲልም ያትታል መግለጫው፡፡

የሕዋ  የውጊያ ምኅዳር በዓለም አዲስ ሊባል የሚችል የውጊያ ዓውድ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2018 የአሜሪካ መከላከያ ኃይል (ፔንታጎን) የሕዋ ውጊያ ቡድን የፔንታጎን ስድስተኛ አካል ሆኖ እንዲቋቋም አዘው ነበር፡፡

ሕዋ አንዱ የጦር ዓውድማ ተደርጎ የሚቆጠር ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ. በ1967 የተፈረመና ጨረቃን ጨምሮ ሌሎች የሕዋ አካላት ላይ የጦር ሠፈር መመሥረትም ሆነ መሣሪያ መሞከር የሚከላከል ዓለም አቀፍ ስምምነት አለ፡፡ አሜሪካ የዚህ ስምምነት ፈራሚ ስትሆን ኢትዮጵያን በሚመለከት ግን የወጣ መረጃ የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...