Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ምርት ገበያው በጥቅምት ወር ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ቡና አገበያየ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በተጠናቀቀው የጥቅምት ወር በኢትዮጵያ የምርት ገበያ የቡና ግብይት መጠን ከቀዳሚው ወር በ74 በመቶ ጭማሪ የታየበት ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ የምርት ገበያ የጥቅምት ወር ግብይቱን በተመለከተ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በቡና ግብይት ዋጋ በ76 በመቶ ጨምሮ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የቡና ግብይት ተፈጽሟል፡፡

በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም. ምርት ገበያው 35,221 ቶን ምርት ገበያ ላይ የዋለ ሲሆን፣ በዚህ ግብይት 25,577 ቶን ቡና፣ 7,480 ቶን ሰሊጥና 2,165 ቶን ነጭ ቦሎቄ ወደ ምርት ገበያው ቀርቦ በ2.2 ቢሊዮን ብር ተገበያይቷል፡፡

በምርት ገበያው መረጃ መሠረት በ23 ቀናት ውስጥ ቡና የግብይቱን 72.6 በመቶ በመጠንና 83.9 በመቶ በዋጋ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል፡፡ ይህ የግብት መጠን ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር የቡና ግብይት መጠን በ74 በመቶ፣ የግብይት ዋጋው ደግሞ በ76 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በቡና ግብይት ውስጥ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ቡና የግብይቱን 66 በመቶ በመጠንና 68 በመቶ በዋጋ የያዘ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ቡናና ስፔሻሊቲ ቡና ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል ተብሏል፡፡

የጥቅምት ወር የቡና ግብይት እንደሚያሳየው 16,236 ቶን ያልታጠበ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ቡና በ1.2 ሚሊዮን ብር የተገበያየ ሲሆን፣ ያልታጠበና ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ቡና በ46.3 ሚሊዮን ብር ተገበያይቷል፡፡ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል 6,394 ቶን ቡና በ402.7 ሚሊዮን ብር ግብይት እንደተፈጸመ የምርት ገበያው አስታውቋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ያልታጠበ የአገር ውስጥ ቡና 58 በመቶ የግብይት መጠን በማስመዝገብ ቀዳሚ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በወሩ ውስጥ 2,230 ቶን ስፔሻሊቲ ቡና በ185.1 ሚሊዮን ብር የተገበያየ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 305 ቶን ያልታጠበ ስፔሻሊቲ ቡና በ37.3 ሚሊዮን ብር፣ 1,925 ቶን የታጠበ ስፔሻሊቲ ቡና በ147.8 ሚሊዮን ብር ተገበያይቷል፡፡

ከቡና ሌላ የሰሊጥ ግብትን በተመለከተ ምርት ገበያው በላከው መረጃ በጥቅምት ወር 7,480 ቶን ሰሊጥ በ318.8 ሚሊዮን ብር የተገበያየ ሲሆን፣ የሁመራ/ጎንደር ሰሊጥ በግብይት መጠን 73 በመቶ፣ በዋጋ 76 በመቶ በመያዝ ከሰሊጥ አንደኛውን ደረጃ ይዟል፡፡ ካለፈው ወር ግብይት ጋር ሲነፃፀር የግብይት ዋጋው በ224 በመቶ እንዲሁም የግብይት መጠኑ በ263 በመቶ አድጓል፡፡

በቦሎቄ ግብይት 2,165 ቶን ነጭ ድብልብል ቦሎቄ በ29.9 ሚሊዮን ብር ተገበያይቷል፡፡ ካለፈው ወር ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 63 በመቶ በመጠንና 66 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ መረጃው ይገልጻል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች