የአጠቃላይ ትምህርት አግባብነትና ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 1,407 የግልና የመንግሥት ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ባደረገው የውጭ ኢንስፔክሽን ጥናት፣ 1,106 ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን አስታወቀ፡፡
በትምህርት ቤቶች ላይ የተሠራውን ኢንስፔክሽን አስመልክቶ ዛሬ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኤጀንሲው ዳይሬክተር ወ/ሮ ብሩክነሽ አርጋው እንደገለጹት፣ በ2010 ዓ.ም. በተሠራው ኢንስፔክሽን በቅድመ መደበኛ 601፣ በመጀመሪያ ደረጃ 419 እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ 86 ትምህርት ቤቶች በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ አይደሉም፡፡
ኤጀንሲው ምዘና ካደረገባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል 78.6 በመቶ ብቁ አለመሆናቸውን ያመላክታል፡፡