Wednesday, July 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በ200 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል ተመረቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በጃፓን መንግሥት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ በአማራ ክልል የተገነባው ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ተመረቀ፡፡

ፎገራ ብሔራዊ ሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል፣ በአገሪቱ ለሩዝ እርሻ ተስማሚነቱ ለሚነገርለት 30 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ለማልማት ብሎም ከውጭ ለሚገባውና ከ300 ሺሕ ቶን በላይ ከውጭ የሚገባ ሩዝ ምርትን ለመተካት ተስፋ የተጣለበት ብሔራዊ የሩዝ ማዕከል የአገሪቱ 18ኛው የግብርና ምርምር ማዕከል ሆኖ ሐሙስ፣ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቋል።

አማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር ዴኤታው ካባ ኡርጌሳ (ዶ/ር) ከጃፓን አምባሳደር ዳያሱኪ ማትሱናጋ እንዲሁም ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር በመሆን  ማዕከሉን መርቀዋል።

ቶ ገዱ እንደገለጹት፣ የፎገራ ምርምር ማዕከል እንዲገነባ የአካባቢው አርሶ አደሮች 33 ሔክታር መሬት ለመንግሥት ሰጥተዋል። የፎገራ መሬት በአብዛኛው ረግረግማ በመሆኑ ሳቢያ፣ ውኃ ስለሚተኛበት የሩዝ ምርት ከመምጣቱ በፊት ለእርሻ ሥራ ብዙም አመቺ አልነበረም። በአሁኑ ወቅት ግን በመላው አገሪቱ ከለማው 53 ሺሕ ሔክታር የሩዝ መሬት ውስጥ 75 በመቶው እንዲሁም ከተመረተው 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 80 በመቶው በአማራ ክልል በተለይም በፎገራ አካባቢ እንደለማ ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።

የሩዝ ምርምር ማዕከሉ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲገነባ፣ ከዚህ ውስጥ 170 ሚሊዮን ብሩን ጨምሮ የቴክኒክና የላቦራቶሪ ቁሳቁሶችን በጃፓን መንግሥት ድጋፍ ተደርጎለታል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች