ተራ የሜዳ አህያ ሰፋፊ ጥቁርና ነጭ መስመሮች፣ በተለይ ከወደ ታፋው የሚነሱት የበለጠ ሰፋፊ የሆኑ መስመሮች አሉት፡፡ ወንዱ በአማካይ 250 ኪሎግራም፣ ሴቷ 220 ኪሎግራም ይመዝናሉ፡፡ ተራ የሜዳ አህያ የተሳካለት ሣር በል ነው፡፡ ዛፍ ከሌለባቸው የአጫጭር ሣር ሜዳዎች፣ ትልልቅ ሣር ባለባቸው ስፋራዎችና፣ ገላጣነት ባላቸው ጫካዎችም ይገኛል፡፡ በብዙ የአፍሪካ አገሮች ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ፣ አርባ ምንጭ አጠገብ በሚገኘው የነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ በብዛት ይገኛል፡፡
- ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) «አጥቢዎች» (2000)