Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናቡና ኢንተርናሽናል ባንክና ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሱ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክና ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሱ

ቀን:

የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ለሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለተቋራጭ የገቡትን ዋስትና አልከፍልም ብለውኛል ያላቸውን ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበርና ብርሃን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበርን በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ከሰሰ፡፡

ኢንተርፕራይዙ ከባንኩና ከኢንሹራንስ ኩባንያው ጋር ተቋራጩንም የከሰሰ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ በገቡት ውል መሠረት የተጠየቁትን የዋስትና ማስያዣ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ቢሆንም፣ ምላሽ በማጣቱ የኮንትራት ውሉንና ተገቢ የሕግ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ መብቱን በፍርድ ቤት ለማስጠበቅ ክስ መመሥረቱን ሰነዶቹ ያሳያሉ፡፡

በተቋማቱ ላይ የተመሠረተው ክስ እንደሚያስረዳው ኤፍሬም ታምሩ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ኩባንያ ባለዘጠኝ ፎቅ ሁለት ብሎኮች ለመገንባት፣ ከኢንተርፕራይዙ በተሻሻለ ኮንትራት በ38,292,667 ብር ውል ፈጽሟል፡፡ ግንባታውንም በ520 ቀናት አጠናቆ ለማስረከብ ተስማምቷል፡፡ ተቋራጩ ውሉን ሲፈጽም፣ ቡና ባንክ 7,658,533 ብር፣ ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ ደግሞ የመልካም አፈጻጸም ዋስትና 3,829,266 ብር መስጠታቸውን ኢንተርፕራይዙ በክሱ ዘርዝሯል፡፡

ተቋራጩ ግንባታውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መፈጸም ባለመቻሉ፣ የኢንተርፕራይዙ አማካሪ ድርጅት ኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በተለያዩ ጊዜያት ሁለት ማስጠንቀቂያዎችን መስጠቱንም ክሱ ያብራራል፡፡

ተቋራጩ የተከለሰ ዕቅድ አቅርቦ የግንባታ አፈጻጸሙን እንዲያሻሽልና ግንባታውን በውሉ መሠረት የሚጠይቀውን የግንባታ ዕቃዎች ግብዓት አቅርቦት በማሳየት ጤነኛ የሆነ የገንዘብ ፍሰት የሚያሳይ ዕቅድ፣ የሰው ኃይል፣ ማሽነሪዎችና ሌሎች ለግንባታው የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዲያሟላ አማካሪ ድርጅቱ ምክር የሰጠው ቢሆንም፣ ተቋራጩ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉንና አፈጻጻሙን ማሻሻል ሳይችል የዋስትና ጊዜ ገደቡ መጠናቀቁንም ክሱ ያስረዳል፡፡ ዋስትናውን እንዲያሳድስ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ ኮንትራቱ እንዲቋረጥ ማድረጉንም ክሱ ያብራራል፡፡

በመሆኑም ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ብርሃን ኢንሹራንስና ተቋራጩ በተናጠልና በጋራ የተጠየቀውን ገንዘብ ከእነወለዱ እንዲከፍሉ፣ ኢንተርፕራይዙ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትሐ ብሔር ችሎት ክሱን አቅርቧል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...