Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሲአን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ምክር ቤት የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ እንደሚደግፍ አስታወቀ

የሲአን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ምክር ቤት የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ እንደሚደግፍ አስታወቀ

ቀን:

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ሲዳማ ዞን ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ላለፉት 40 ዓመታት የታገልኩለት ዓላማ በመሆኑ የምደግፈው ዕርምጃ ነው ሲል አስታወቀ፡፡ የሲአን አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በውጭ አገር የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡና እንዲታገሉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ወደ አገር ውስጥ መግባቱን በማስታወቅ፣ ሲዳማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው አስተዋፅኦ የጎላ እንዲሆን ለማድረግም እሠራለሁ ሲል አስታውቋል፡፡

‹‹የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ በተለየ መንገድ የሚረዱ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይሁንና የብሔር ማንነትና ኢትዮጵያዊነት አብረው የሚሄዱ ናቸው ብለን ስለምናምን፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ በመሰጠቱ ከማንም በላይ ዘብ የምንቆምላት ኢትዮጵያ ነች የምትኖረው፤›› ሲሉ፣ የንቅናቄው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ምክር ቤት ሰብሳቢ በዛብህ በራሳ (ዶ/ር) ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

ስለዚህ ይህ ውሳኔ ወደ ተግባር እንዲገባ በፍጥነት ሕዝበ ውሳኔ ተደራጅቶ ሲዳማ ራሱን በራሱ ማስተዳደሩ ዕውን እንዲሆን ጥሪ በማቅረብ፣ ‹‹ሲዳማ የኢትዮጵያ አካል ሆኖ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ያለባት ኢትዮጵያ እንድትኖር፣ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነን፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደጀኔ ወልደ አማኑኤል የብሔር ግጭቶችን በተለይም የወላይታና የሲዳማ ብሔር ግጭቶችን በማነሳሳት የሲዳማን ጥያቄ ሌላ መልክ ለማስያዝ ጥረት የሚያደርጉ አካላት አሉ ካሉ በኋላ፣ ‹‹በመሠረቱ የሲዳማና የወላይታ ፍላጎት ምንም የሚያጋጭ አይደለም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ‹‹ሁለቱም የራሳቸው አስተዳደር ተሰጥቷቸው በሰላም እንድንኖር ነው የምንፈልገው፤›› ብለዋል፡፡

በቀጣይ ምርጫ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ፓርቲያቸው ብቁ ዝግጅት ማድረጉን፣ እንደ ካሁን ቀደሙ አንድ ፓርቲ በበላይነት የሚመራት አገር ስለማትሆን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ጥምረት ፈጥረው ለመሥራት ዓላማ እንዳላቸው፣ ለዚህም ለቀጣዩ ምርጫ እየተዘጋጁ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

የመድረክ አባል የሆነው ሲአን መሥራች የሆኑ ስድስት አባላት ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ያስታወቁት የድጋፍ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣ በተለያዩ አገሮች ያሉና እስካሁን በፖለቲካው በንቃት ሊሳተፉ ያልቻሉ አባላትን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹አሁን በአገሪቱ እያታየ ያለው ለውጥ እንዳይጨናገፍና ዘላቂ እንዲሆን ያለምንም ማለሳለስ የምንደግፈው ነው፤›› ያሉት አቶ ደጀኔ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና ለመንግሥታቸው ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ‹ኤጀቶ› በመባል የሚታወቁት የሲዳማ ወጣቶችን በለውጡ ተጫውተዋል ላሉት ሚናም አመሥግነዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...