Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርበዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የመብት ጥሰት ይቁም!

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የመብት ጥሰት ይቁም!

ቀን:

ለጊዜ ምሥጋና ይግባውና ሴት እህቶቻችን ለዘመናት ባረጀና ባፈጀ ሥርዓት ተፅዕኖ ሥር ወድቀው ከነበሩበት ወቅት ተላቀው አንገታቸውን ቀና በማድረግ እናት አገራችንን በፕሬዚዳንትነት እስከ መምራት ደርሰዋል፡፡ በትግላቸው የተቀዳጇቸውን  ወሳኝ ድሎች እንዳይነጠቁ የሚያካሂዱት አመርቂ እንቅስቃሴ እሰየው ያሰኛል፡፡

በሌላ በኩል ይህንኑ መልካም ጅምር የሚቀናቀን እኩይ ተግባር የምሁራን መፍለቂያ በሆኑት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲፈጸም እያየን ነው፡፡ በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ውስጥ በአንዱ በስፋት ሲንፀባረቅ የምንታዘበው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሴት ተማሪዎችን መብት በመጣስ አደብ ያጡ እብሪተኛ ወንዶች ተማሪዎች ቅጥ ያጣ ትንኮሳ ሲፈጽሙ ይስተዋላል፡፡ የወሲብ ጥያቄያቸው ምላሽ ካላገኘ የሴቶችን ጌጣ ጌጦቻች መንጭቀው የሚወስዱ፣ በማስፈራራት ገንዘብ የሚዘርፉ፣ አለፍ ሲልም ሕግ ለእነሱ ብቻ የቆመ እስኪመስል ድረስ በግልና በቡድን ሴቶችን የሚደፍሩ እንዳሉ ሁሉም የሚያውቀው፣ የሚነጋገርበት ጉዳይ ነው፡፡

- Advertisement -

በእንስትነታቸው ምክንያት በተባእት ወንድሞቻቸው ለዚያውም በገዛ አገራቸው ዋስትናና መድን በመሆን ከለላ የሚሰጣቸውና የሚታደጋቸው አካል በማጣታቸው፣ ሴቶች ተማሪዎች የሚደርስባቸው ጥቃትና ትንኮሳ እየተባባሰ መጥቷል፡፡ ይህንን ሃይ ባይ ያጣ ተፅዕኖና ግፍ አንዳች የሚገታው ሕግ እንዲከበር፣ በሕግ አምላክ ብሎ የሚዳኝ አካል እንዲያየው በማሰብ ጉዳዩ ወደሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አካላት በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም የሚሰጣቸው ምላሽ አጥጋቢ አልሆነም፡፡ ከለላና ጥበቃ ማድረጉ ቀርቶ ለቀረበላቸው እሮሮ ምንም ዓይነት ዕርምጃ ስለማይወሰዱ፣ በሴቶች ላይ  ጥርስ እንዲነስባቸው በማድረግ የጥቃት ዙሩ እንዲከርባቸው የሚያነሳሳ አካሄድ እየተከተሉ ነው፡፡

ሴቶች መግቢያና መውጫ በማጣታቸው ሳቢያ ዓላማ ሰንቀውና ርቀው ስለሄዱበት ትምህርታቸው ሳይሆን፣ ስለዕለት ህልውናቸው በመጨነቅ ከትምህርቱም ከነፍሳቸውም ለመራቅ እየተገደዱ መኖር ከጀመሩ ሰነባበተዋል፡፡ ተምረው ራሳቸውንና  ኢትዮጵያን ይረዳሉ ብለን የላክናቸው ልጆቻችን ዕጣ ፈንታቸው የብልሹ አስተሳሰብና የብልሹዎች ሰለባ በመሆን የትም ባክኖና መክኖ መቅረት እየሆነ ሲቀር ለምን እንደ ተራ ነገር በዝምታ ይታለፋል? የዜጎች ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥበቃ የሚያጎናጽፈው ብሔራዊ ሕጋችን እዚህ አካባቢ ስለምን ይሸርሸር፣ ይሸራረፋል? ኧረ የአገር ያለህ! የሕግ ያለህ!

እስካሁን ላቀረብኩት አቤቱታ ማስረጃ የሚፈልግ አካል፣ በዩኒቨርሲቲው ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት ሴቶች የኢንጂነሪንግ ተማሪዎችን ማነጋገርና መረዳት ይችላል፡፡

(ደራ፣ ከዩኒቨርሲቲው የመብት ተቆርቋሪዎች)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...